በሶርያ የተጠናከረው የርስ በርስ ጦርነት | ዓለም | DW | 27.08.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

በሶርያ የተጠናከረው የርስ በርስ ጦርነት

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ከዋና ከተማዋ ከደማስቆ አጎራባች የምትገኘው የዳርያ ከተማ ቢያንስ የ320 ሰዎች አስክሬን መገኘቱን የአረቡ አለምና አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በመዘገብ ላይ ናቸው ፡፡

ብዙዎቹም ጭንቅላታቸው ላይ በጥይት ተመተው እንደተገደሉ ነው የሚሰማው። የሶሪያ መንግስት ነጻ የመገናኛ ብዙሃን ወደ ቦታው እንዳይሄዱ በመከልከሉ የተባለውን ጭፍጨፋ ከነጻ ምንጭ ለማረጋገጥ ከባድ አድርጎታል።
በትናንትናው ዕለት በችግሩ ዙሪያ የተጠየቁት የአረብ ሊግ የበላይ ሃላፊ ነቢል አል አረቢ ሁከቱ ከከባድ ሁከት ወደ አስከፊ ፍጅት መሸጋገሩን በመግለፅ፤ አረብ ሊግ ከአዲስ የመንግስታቱ ልዩ ልኡክ እና ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ችግሩን ለመፍታት የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ነብዩ ሲራክ ከሳውድ አረቢያ ያጠናቀረው ዘገባ አለ።

ነብዩ ሲራክ

ክደት አበበ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic