በሶርያ አስከፊዉ አመጽ | ዓለም | DW | 05.02.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ዓለም

በሶርያ አስከፊዉ አመጽ

ሶሪያ ውስጥ እስካሁን አስከፊው እንደሆነ በተነገረለት በመንግሥቱ ወታደሮች በተቃዋሚዎች መካከል በተካሄደ ውጊያ በዛሬው ዕለት ቢያንስ 200 ሰዎች እንደተገደሉ ተነገረ።

የዓማጺያኑ መናኸሪያ የሆነችው ሆምስ ሌሊቱን ሙሉ በታንኮችና ሌሎች ከባድ መሣሪያዎች ስትደበደብ ማደሯን የዓይን ምስክሮች አስረድተዋል። ይህ በዚህ እንዳለ መንግሥትና ተቃዋሚዎች ጥፋቱን በማድረስ እርስበርስ በመወናጀል ላይ ናቸው። ተያይዞ የደረሰ ዜና እንዳመለከተው የሶሪያ መንግሥት ጦር በሌሎች የአገሪቱ ከተሞችም በተቃዋሚዎች ላይ እየዘመተ ነው። የዳማስቆስ መንግሥት በበኩሉ ድርጊቱ የታጠቁ ሽብርተኞች በዛሬው ምሽት ኒውዮርክ ውስጥ በታሰበው የተባበሩት መንግሥታት ጸጥታ ም/ቤት የሶሪያ ውሣኔ ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ የሚወስዱት ዕርምጃ ነው ብሏል። ሩሢያ በፊናዋ ውሣኔውን በቬቶ ድምጽ እደምትገታ ከወዲሁ አሰጠንቅቃለች። በሆምስ የተፈጸመው ግድያ ዜና እንደተሰማ ቁጣ ያደረባቸው የሶሪያ ተወላጆች በካይሮ፣ በለንደን፣ በኩዌይትና በበርሊን ወደሚገኙት የሶሪያ ኤምባሲዎች በማምራት በከፊል ሃይል የተመላበት ተቃውሞ አሰምተዋል። የሆምስ ግድያ በዓለም ዙሪያ እየተኮነነ ሲሆን ቱኒዚያ በበኩሏ ለሶሪያ አመራር ዕውቅና ለመንፈግና አምባሣደሯን ለማስወጣት ምርመራ መጀመሯን አስታውቃለች።

አዜብ ታደሰ

መስፍን መኮንን

 • ቀን 05.02.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/13xAi
 • ቀን 05.02.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/13xAi