በሶርያና በእስራኤል የወደፊት ግንኙነት ላይ ያተኮረ ጉባዔ በደማስቆ | ፖለቲካ | DW | 04.09.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ፖለቲካ

በሶርያና በእስራኤል የወደፊት ግንኙነት ላይ ያተኮረ ጉባዔ በደማስቆ

የሶርያ፦ የፈረንሳይ፡ የቱርክና የቓታር መሪዎች ፤ ፕሬዚደንት በሺር አል አሳድ፤ ፕሬዚደንት ኒኮላ ሳርኮዚ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ረቸፕ ጠይብ ኤርዶኻንና አሚር ሼኽ ሀማድ ቢን ኻሊፋ አል ጣኒ ዛሬ በሶርያ መዲና ደማስቆ ያካሄዱት ጉባዔ የቆየው አንድ ሰዓት ብቻ ቢሆንም፡ ጉባዔው ለሶርያ ትልቅ ትርጓሜ ይዞዋል።

ፕሬዚደንት አሳድና የፈረንሳዩ አቻቸው ሳርኮዚ

ፕሬዚደንት አሳድና የፈረንሳዩ አቻቸው ሳርኮዚ

ምክንያቱም፡ እስከአሁን ከሞላ ጎደል የተገለለችው ሶርያ ለመካከለኛው ምስራቅ ሰላም በሚወርድበተ ጥረት ላይ ከፍተኛ ሚና ከያዙ የተለያዩ ሀገሮች ጋር በአንድ ጠረጴዛ ዙርያ እንድትቀመጥ አስችሎዋታል። የዚሁ ጉባዔ የሩቅ ዓላማ በሶርያና በእስራኤል መካከል መቀራረብ ሊኖር የሚችልበትን ዘዴ ማፈላለግ ነበር።