በሶማልያ የአለም የምግብ ፕሮግራም ችግር | የሶማልያ ውዝግብ | DW | 18.10.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የሶማልያ ውዝግብ

በሶማልያ የአለም የምግብ ፕሮግራም ችግር

በኢትዮጽያ የጦር ሰራዊት የሚታገዘዉ የሶማልያ የሽግግር መንግስት ጦር ሰራዊት፣ በመቅዲሾ የሚገኘዉን የተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤት መዉረራቸዉ ተገለጸ፥ በመቅዲሾ የሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ወታደሮቹ በቅጽር ግቢዉ የአለም የምግብ ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣን ማሰራቸዉን አዣንስ ፍራንስ ፕሪስ ዘግቦአል።

WFP በእርዳታ ላይ

WFP በእርዳታ ላይ

30 ግድም የሚሆኑ የታጠቁ የሶማልያ የሽግግር መንግስት ወታደሮች በሁለት የወታደር ተሽከርካሪ ተጭነዉ በመቅዲሾ በሚገኘዉ የተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤት ቅርንጫፍ ጥሰዉ በመግባት በድርጅቱ የአለም የምግብ ድርጅት ቢሮ ተጠሪን Idris Mokamed Osman ን ይዘዉ ፕሪዝደንቱ መኖርያ አቅጣጫ መሰወራቸዉ ተገልጾአል። ወታደሮቹ ግለሰቡ ቢሮ ገብተዉ ሲወስዱዋቸዉ መጣራት ያለበት ነገር አለ ማለታቸዉን የድርጅቱ ተጢሪዎች ተናግረዋል።

ዋና መቀመጫዉን በጣልያን ሮም ያደረገዉ የአለም የምግብ ድርጅት ቢሮ ቃል አቀባይ ቤሪ ኬም በሶማልያ የሽግግር መንግስት ወታደሮች የድርጅታቸዉ ተጠሪ ወደ አልታወቀ ቦታ መያዙን ስለማወቃቸዉ በስልክ ላቀረብንላቸዉ ጥያቄ

(ግለሰቡ በመንግስት ወታደሮች መያዛቸዉን በግልጽ የምናዉቀዉ ወይም የተገለጸልን ነገር የለም። ነገር ግን የመስራቤታችን ባልደረባ Idris Mokamed Osman ን በዉል ባላወቅናቸዉ የጦር ሃይሎች መወሰዳቸዉን ነዉ ጉዳዩን በማጣራት ላይ ነን)

የሶማልያ በየግዜዉ የሚያገረሸዉ እና ማለቅያ ያጣዉ ዉጥረት በተባበሩት መንግስታት ስር በአገሪቷ የነበሩ በርካታ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች አገሪቷን ጥለዉ እንዲወጡ ተገደዋል። በአሁኑ ወቅት በሶማልያ የሚገኙ አንዳንድ የእርዳታ ድርጅቶች በአካባቢዉ ተጠሪዎች ቢንቀሳቀሱም በየወቅቱ የሚቀሰቀሰዉ ዉጥረት ምክንያት ስራቸዉን ለማቆም በመገደድ ላይ ይገኛሉ።

በመቅዲሾ የሚገኘዉ እና ስሙን እንዳይጠቀስ የሚፈልገዉ ጋዜጠኛ በበኩሉ በመቅዲሾ የአለም ምግብ ድርጅት ከፍተኛ ተጠሪ በፓሊሶች ተይዘዉ ወደ አልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸዉን በመቅዲሾ መሰማቱን ገልጾአል።

ትናንት በተለይ በደቡባዊ መቅዲሾ በኢትዮጽያ የጦር ወታደሮች በሚታገዙት በሶማልያ የሽግግር መንግስት ወታደሮች እና በእስላማዊ ሽምቅ ተዋጊዎች መካከል በተነሳ ከፍተኛ ጦርነት በርካታ ሲቢሎች መመታቸዉን በመቅዲሾ የሚገኘዉ ጋዜጠኛ አራግጦልናል። ጦርነቱ በከባድ መሳርያ የተሰማበት ለሊቱን ቀጥሎ ቆይቷል።

(አስር ያህል ሲቢሎች ሞተዋል በርካቶች ቆስለዋል። በግጭቱ ምን ያህል ወታደሮች እንደሞቱ ግን በዉል አይታወቅም በርግጥ ከሶማልያም ከኢትዮጽያም ወገን ወታደር ሳይሞት አልቀረም)

በመቀጠል ዛሪ በባይድዋ በፕሪዝደንት አብዱላሂ ዩሱፍ እና በጠቅላይ ሚኒስትር መሃመድ ጌዲ መካከል የተፈጠረዉን አለመግባባት ለመቅረፍ ዝግጅት መካሄዱን ሲገልጽልን ከዝግጅቱ በኻላ ጠቅላይ ሚኒስትር መሃመድ ጌዲ ለችግሩ መፍትሄ ለመሻት ወደ አዲስ አበባ መጓዛቸዉን ገልጾልናል።