በሶማልያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት | የሶማልያ ውዝግብ | DW | 19.03.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የሶማልያ ውዝግብ

በሶማልያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሶማልያ ያለዉን የሰብዓዊ መብት ረገጣ ነቀፈ። ድርጅቱ ይህንን ነቀፊታ ያሰማዉ KISIMA የተባለዉ የሰላም እና የልማት ድርጅት መሪ የነበሩትና በሶማልያ ለሰዉ ልጅ መብት በመቆርቆር ታዋቂ የነበሩት Isse Abdi ባልታወቀ ታጣቂ ተገለዉ መገኘታቸዉ ከተሰማ በኻላ ነዉ

የሶማልያን ፖሊስ በመቅዲሾ

የሶማልያን ፖሊስ በመቅዲሾ

ይህን አስታኮ ህዉከት እና ግጭት እየተበራከተ በመጣበት በሶማልያ በሚገኙ የእርዳታ ድርጅት ሰራተኞች፣ ኢላማ እየሆኑ ነዉ ሲል አስጠንቅቆአል። ይህ በንዲህ እንዳለ በትናንትናዉ እለት የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ልኡካን ቡድን ባይደዋ መግባታቸዉ ታዉቋል። ልኡካኑ ከተለያዩ የአሪገቷ ባለስልጣናት፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጌዲ እንዲሁም ከሶማልያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢስማኢል ቡባ ጋር የተባበሩት መንግስታት ጦር ሰራዊት ከስድስት ወር በኳላ በሶማልያ ሊሰፍር የሚችለበት ሁኔታ ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል። Eric Laroche ን አዜብ ታደሰ በስልክ አነጋግራአቸዉ ነበር