በስኬትቦርድ ከአዲስ አበባ እስከ ሀረር ጉዞ | ባህል | DW | 26.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

በስኬትቦርድ ከአዲስ አበባ እስከ ሀረር ጉዞ

ካሳለፍነው ማክሰኞ ጀምረው ሰባት ኢትዮጵያዊ እና የውጭ ዜግነት ያላቸው ወጣቶች ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ ሀረር ጎዞ ጀምረዋል። ጉዞዋቸው በመኪና ወይንም በብስክሌት አይደለም፤ በስኬትቦርድ ነው። ስለዚህ ረዥም ጉዞ እና የስኬት ቦርድ አነዳድ የዛሬው የወጣቶች አለም ትኩረት ይሆናል።

ትንሽ ነው ከጠፍጣፋ እንጨት የተሰራ፣አራት ጎማዎች ያሉት ምናልባትም መካከለኛ መክተፊያ ያክላል። ሰሞኑን ፤ አዲስ አበባን ከሀረር ከሚያገናኘው ጎዳና ላይ እንደዚህ አይነት እንጨት ላይ ቆመው ወይንም በአንድ እግራቸው እየገፉና ጣውላው ላይ ዘለው እየቆሙ የሚጓዙ ወጣቶች አይታችሁ ከሆነ ፤ የስኬትቦርድ ነጂዎች ናቸው። ካሳለፍነው ማክሰኞ ጀምረው ከአዲስ አበባ -ሀረር ጉዞ ጀምረዋል። ትናንት አዋሽ ደርሰው ዕረፍት ሲያደርጉ ከጉዞ ተካፋዮቹ መካከል ሁለቱን በስልክ አነጋግረናቸዋል።

የ 16 አመቱ አቤነዘር ከሁለት አመት በፊት ነው እስኬትቦርድ መንዳት የተማረው። ዛሬ የዚህ ጉዞ ተካፋይ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ስኬትቦርድ የምንነዳ ከሰላሳ በላይ እንሆናለን ይላል አቤነዘር። ይህን ብዙም ያልተለመደ የአነዳድ ዘዴ በሰሞኑ ጉዞዋቸው ለሌሎች ለማስተዋወቅ መንገድ ከፍቶላቸዋል።

በዚህ ጉዞ ከአቤነዘር ሌላ 6 የስኬትቦርድ ነጂዎች አሉ። ሚካኤል ፋሲል ግን ዛሬ ምድቡ በቪዲዮና ፎቶ ማንሳት ስራ ላይ ነው። ሚካኤል በዚህ ጉዞው የቪዲዮ ዘገባውን ሲያሰናዳ እንደው የሰዉን አመለካከት እንዴት እንዳገኘው ገልፆልናል።

ከ500 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት በሰው ሀይል በሚንቀሳቀስ ስኬትቦርድ መንዳት መቼም ብዙ ጉልበት መጠየቁ አይቀሬ ነው። ትንሽ ብያደክምም መንገድ ላይ የምናያቸው ደስ የሚሉ ነገሮች ይበልጥ ቀጥለን እንድነዳ ያበረታቱናል ይላል አቤነዘር። ምባልባት ነገ አልያም እሁድ ተጓዦቹ እና አብሮዋቸው ያሉት አጃቢዎች ሀረር እንደሚደርሱ ተስፋ ያደርጋሉ።

እስካሁን ስለነበራቸው ጉዞ ማወቅ ከፈለጋችሁ የድምፅ ዘገባውን ይጫኑ።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic