በስህተት የተገደለው ኢትዮጵያዊ ጉዳይ እና የፍትህ ጥያቄ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 27.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

በስህተት የተገደለው ኢትዮጵያዊ ጉዳይ እና የፍትህ ጥያቄ

የሞገስ ስም በስህተት ከተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ በመገኘቱ ወንድሙ እና ጓደኞቹ መንግሥት ፍትህ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ነው ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:14

በስህተት የተገደለው ኢትዮጵያዊ ጉዳይ እና የፍትህ ጥያቄ

           
ከዛሬ 27 ዓመት በፊት ለንደን ውስጥ የራሱን ህይወት አጥፍቷል የተባለ ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ፍትህ እንዲያገኝ ቤተሰቦቹ እና ወዳጆቹ በድጋሚ ጠየቁ ። የሟች ወንድም እንደሚሉት ፣ፖሊስ ሞገስ አባይ የተባለው ወንድማቸው በጎርጎሮሳዊው ሰኔ 30 1990 ከሚኖርበት ህንፃ ራሱን ወርውሮ ህይወቱን አጥፍቷል ቢልም በወቅቱ የተገኙት መረጃዎች ግን አጠራጣሪ ነበሩ ። የአይን ምስክሮችም ሆኑ የሟች ወንድም ሞገስ ያኔ  የራሱን ህይወት ማጥፋቱን የሚጠቁም ማስረጃ እንዳላዩ ነው የሚናገሩት ። በቅርቡ ደግሞ የሞገስ ስም በስህተት ከተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ በመገኘቱ ወንድሙ እና ጓደኞቹ መንግሥት ፍትህ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ነው ። ዝርዝሩን የለንደንዋ ወኪላችን ሀና ደምሴ ልካልናለች ። 
ሀና ደምሴ 
ኂሩት መለሰ 
ነጋሽ መሐመድ 

Audios and videos on the topic