በሳይንስ የዘንድሮ የኖቤል ተሸላሚዎች | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 08.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

በሳይንስ የዘንድሮ የኖቤል ተሸላሚዎች

ከሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ወደ ደቡብ እስከ ምድር ሰቅ የሚዘልቁና ወደመጡበት ሳይደናገሩ የሚመለሱ አእዋፍ ምንቃራቸው አጠገብ በቀኝ በኩል አቅጣጫ አመላካች የተፈጥሮ «ኮምፓስ» አላቸው። የሌሊት አእዋፍ ፣ ዓይን ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ አቅጣጫ ጠቋሚ አላቸው።

ሌሎች እንስሳትና አሦችም እንዲሁ!

ሰውስ? --ጤናይስጥልኝ እንደምን ሰነበታችሁ? በሳይንስ የዘንድሮውን የኖቤል ሽልማት አሸናፊዎችና ፣ ለሽልማት ያበቃቸውን ጉዳይ አጠር አድረገን ለመዳሰስ እንሞክራለን። ሰኞ የሕክምና ፤ ትናንት የፊዚክስ ፤ ዛሬ ደግሞ የሥነ ቅመማ ውድድር አሸናፊዎች ማንነት ታውቆአል። በፊዚክስ እንጀምር----

ሁለቱም ጃፓናውያን የፊዚክስ ተመራማሪዎች ናቸው ፣ የ 85 ዓመቱ አዛውንት ኢሳሙ አካሳኪና ፤ የ 54 ዓመቱ ገልማሣ ፣ ሂሮሺ አማኖ! 3ኛውም ቢሆን በዜግነት አሜሪካዊ ይሁኑ እንጂ በትውልድ እርሳቸውም ጃፓናዊ ናቸው። የ 60 ዓመቱ የፊዚክስ መምህር ሹጂ ናካሙራ! ከእስቶክሆልም የካሮሊንስላካ የሳይንስ አካዳሚም ሆነ ተቋም እንዳስታወቀው፤ ጃፓናውያኑ በፊዚክስ የዘንድሮው የኖቤል ሽልማት አሸናፊዎች ለመሆን በቅተዋል።

3 ቱ ተማራማሪዎች የመጀመሪያውን ሰማያዊ ብርሃን ፈንጣቂ ኤሌክትሪክ አስተላላፊ መሳሪያ ግኝት ይፋ ያደረጉ እ ጎ አ በ 1986 ዓ ም ነው። ኤሌክትሪክ አስተላላፊና ብርሃን አንጸባራቂ ዱቄት መሰልም ሆኑ ጠጣር አካላት፤ ከተለመዱት ለመብራት ከሚገለግሉ ፍም መሰልና ኃይል ቆጣቢ አምፑሎች በላቀ ሁኔታ ይበልጥ ኃይል ቆጣቢ ፣ ለረጅም ጊዜ ሳይበላሹም ሆነ ሳይቃጠሉ የሚያገለግሉ፤ በተጨማሪም ለተፈጥሮ አካባቢ ተስማሚዎች ናቸው።

የጃፓናውያኑ ምርምር ሰው ሠራሽ የኤሌክትሪክ ብርሃን አብዮት እንዲካሄድ አብቅቷል ነው የሚባለው። የኖቤል የሽልማት ሰጪ ኮሚቴ ባልደረባ፣ ፔር ዴልሲንግ እንዳሉት፣ ቀይና አረንጓዴ ብርሃን ፈንጣቂ ኤሌክትሪክ አስተላላፊ መሣሪያዎች ገበያ ላይ ከዋሉ ዓመታትን ቢያስቆጥሩም ሰማያዊ ብርሃን አንጻባራቂውም ሆነ ፈንጣቂው በጃፓናውያኑ ተመራማሪዎች በኩል ሊከሠት መቻሉን ነው የዘንድሮውን ሽልማት አሸናፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ ባደረጉበት ሰዓት የገለጡት።

ቀይ ፤ አረንጓዴ እና ሰማያዊ ፣ --እነዚህ ሦስት ቀለማት ደማቅ ፣ ፍንትው ያለ ብርሃን ነው የሚፈነጥቁት። ለተፈጥሮ አካባቢም እጅግ ተስማሚ ነው --ኃይል ቆጣቢ ነውና! እ ጎ አ በ 1986 ዓ ም የተሳካላቸው ግኝት፤ ከተለመደው የሚግል አምፑል የላቀ ብቃት ያለው ብርሃን ሰጪ ነው። የኖቤል ሽልማት ሰጪ ኮሚቴ ባልደረባ ፔር ዴልሲንግ---

«ይህ የብርሃን ፈንጣቂ ቁስ (LED) ሥነ ቴክኒክ አሮጌ ቴክኖጂዎችን በመተካት ላይ ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ ብዙዎች ይዘውት የሚዞሩ ሲሆን ቴክኖሎጂው በእርስዎ ኪስም ይገኛል።»

ዴልሲንግ ይህን ሲሉ፣ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የእጅ ስልኮችን --«ስማርትፎንስ» ን ማመላከታቸው ነው። ስማርትፎንስ ያለ LED ሊታሰቡ ባልቻሉ ነበር። የኖቤል ኮሚቴ እዚህ ላይ፤ በተለይ በዓለም ዙሪያ የኤልክትሪክ አገልግሎት የማያገኘውን ሕዝብ ይዞታ ማሰላሰሉ አልቀረም። ለዚያ ህዝብም ፣ ኃይል ቆጣቢው LED መብራት ከጨለማ አውጥቶ በብርሃን የሚያኖር ይሆናል።

ጃፓናውያኑ ሳይንቲስቶች እንዲገኝ ያበቁት ሰማያዊ መብራት ሙቀት የለውም፣ ይሁንማ ሙቀትንና ብርሃንን ማጣመር የሚያዳግት አይደለም። በዚህ ረገድ እንዲያውም ጥቂት ጀርመናውያን ተመራማሪዎች እ ጎ አ በ 2013 «ዶቸ ሱኩንፍት ፕራይስ» ለተሰኘው ሽልማት በእጩነት ቀርበው እንደነበረ የሚታወስ ነው። አምና ፤ ለአብዝኃው፣ ውስብስብ የሆነውን የፍጥረተ- ዓለም መሠረት የሆነውን «የእግዚአብሔር ቅንጣት» ወይም (የ ሂግስ የአቶም ኢምንት ቅንጣት) የተሰኘውን ለማግኘት ከአያሌ ዓመታት በፊት በነባቤ ቃል የተነተኑት የብሪታንያው የፊዚክስ ተመራማሪ ፒትር ሂግስና ቤልጂጋዊው ባልደረባቸው ፍርንሷ ኤንግለርት መሸለማቸው የሚታወስ ነው። ነባቤ- ቃሉን LHC በተሰኘው የአቶም ጨፍላቂ መሣሪያ አጋዥነት በተግባር ያሳየ በፈረንሳይና በስዊትስዘርላንድ ድንበር አካባቢ በሚገኘው የአውሮፓውያን የአቶም ምርምር ተቋም ነው።

ትናንት ፤ እስቶክሆልም፣ የስዊድኑ አካዳሚ ካሮሊንስካ ተቋም በህክምና የዘንድሮ የኖቤል አሸናፊዎችን ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

አሸናፊዎቹ፤ የአእምሮ ተማራማሪ የሆኑት የዩናይትድ ስቴትሱ ጆን ኦ ኪፍና 2ቱ የኖርዌይ ተወላጆች ባልና ሚስት ተማራማሪዎች፣ ሜይ-ብሪት ሞዘርና ኤድቫርድ ሞዘር መሆናቸው ታውቋል። ለሽልማት አሸናፊነት ያበቃቸው፤ በአንጎል ውስጥ ሕዋሳት ቦታ ወይም አቅጣጫ የሚይዙበትን ሥርዓት በምርምር ለማሳወቅ በመቻላቸው ነው።

ጆን ኦ ኪፍ እ ጎ አ በ 1971 ፤ ሜይ ብሪት ሞዘርና ኤድቫርድ ሞዘር ደግሞ እ ጎ አ በ 2005 ነው አንጎል ውስጥ በሞተር መሰል ሕዋሳት አማካኝነት ከ ኦ ኪፍ ምርምር ጋር የሚጣጣም ውጤት ማስመዝገብ የቻሉት።

አንጎል ውስጥ የሠራ አካላትን እንቅሥቃሴና አቅጣጫ አመላካች የሆኑ ሕዋሳትን ተለይተው በመታወቃቸው፣ የማስተዋል ችሎታ የሚያሳጣውን ወይም የሚያሥረሳውን በሽታ (አልትስሃይመርን) ምንነትና ፈውሱንም ለመሻት በሚደረግ ጥረት ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ነው የታሰበው።

እ ጎ አ በ 2050 የአልትስሃይመር ሕሙማን ቁጥር አሁን ካለው 44 ሚሊዮን በ3 እጥፍ ገደማ እንደሚጨምርና 135 ሚሊዮን ገደማ እንደሚደርስ ነው የሚገመተው። ሽልማቱን መነሻ በማድረግ ስለምርምሩ ውጤት ጠቃሚነት የአእምሮ ጉዳይ ሳይንቲስት ፣ ፕሮፌሰር ኦሌ ኪን ---

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች