በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሮሮ | ኢትዮጵያ | DW | 14.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሮሮ

ሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፓስፖርታቸውን ለማሳደስ ወይም በሌላ ለመቀየር ረጅም ጊዜ በመውሰዱ መቸገራቸውን ገለጹ። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ሳዑዲ አረቢያ በተለይም ጂዳ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ቆስላ አሮጌ ፓስፖርታቸዉን ሰብስቦ አዲሱን ግን ለረጅም ጊዜ አልሰጣቸዉም።

በዚሕም ምክንያት የመኖሪያ ፍቃዳቸዉ ጊዜ ማለፉን ወይም ሊያልፍ መቃረቡን ይናገራሉ። እንደሚሉትም ፓስፖርታቸውን እንዲታደስ ወይም እንዲቀየር ሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የጠየቃቸውን ገንዘብ ቢከፍሉም፤ የታደሰዉን ፓስፖርት ለማግኘት ከአምስት ወራት በላይ ጠብቀዋል። እስካሁን አላገኙትም።

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic