በሱዳን ፕሬዚደንት ላይ የተላለፈው የእስር ማዘዣና የዐረቡ ዓለም አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 05.03.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በሱዳን ፕሬዚደንት ላይ የተላለፈው የእስር ማዘዣና የዐረቡ ዓለም አስተያየት

በዘ ሄግ ኔዘርላንድስ የሚገኘው ዓለም አቀፉ የወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት በሱዳን ፕሬዚደንት ኦማር ሀሰን አል በሺር ላይ ያስተላለፈው የእስር ማዘዣ ከያቅጣጫው የተለያየ የድጋፍና የተቃውሞ አስተያየት አስከትሎዋል።

default

የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በሱዳን መንግስትና በዳርፉር የተጀመረውን የሰላም ድርድር የሚያሰናክል ነው በሚል የተለያዩ ዐረባውያት ሀገሮች መሪዎችና ህዝቦች ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ነው። የዐረቡ ሊግ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሊቀየር የሚችልበትን መንገድ እንደሚፈልግ ትናንት በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ በኋላ አስታውቋል። የሱዳን ህዝብ የዳርፉር ዓማጽያንና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የደገፉትን የፍርድ ቤቱን የእስር ማዘዣ በመቃወም ትልቅ ሰልፍ አካሂዶዋል። ነቢዩ ሲራክ

AA/TY