1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሰንዳፋ ታስረው የነበሩ ጋዜጠኞች ተለቀቁ

ሰኞ፣ ግንቦት 19 2011

ባለፈው አርብ በኦሮሚያ ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው የአሃዱ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ ታምራት አበራ ዛሬ መለቀቁን ጣቢያው አስታውቋል። በሰንዳፋ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው ታምራት ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተለቀቀው በመታወቂያ ዋስ መሆኑንም ሬድዬ ጣቢያው ገልጿል።

https://p.dw.com/p/3JFQT
Äthiopien Eröffnung Ahadu Radio
ምስል DW/Y. G. Egziabhare

በሰንዳፋ ታስረው የነበሩ ጋዜጠኞች ተለቀቁ

ባለፈው አርብ በኦሮሚያ ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው የአሃዱ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ ታምራት አበራ ዛሬ መለቀቁን ጣቢያው አስታውቋል። በሰንዳፋ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው ታምራት ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተለቀቀው ፍርድ ቤት ሳይቀርብ፣ በመታወቂያ ዋስ መሆኑንም ሬድዬ ጣቢያው ገልጿል።

ጋዜጠኛ ታምራት የታሰረው በሰንዳፋ በኬ 02 ፖሊስ ጣቢያ የፖሊስ አባላት ባለፈው አርብ ግንቦት 16 ቀን 2011 ዓ.ም መሆኑን የአሃዱ ሬድዮ ጣቢያ በዛሬው መግለጫው ጠቅሷል። የሰንዳፋ በኬ 02 ፖሊስ ጣቢያ አቃቤ ህግ የአሃዱ ሬድዮ ጣቢያ ስራ አስኪያጅ፣ ምክትል ዋና አዘጋጅ፣ የዜና ክፍል ኃላፊ እና ኤዲተር ከነገ በስቲያ ረቡዕ በጽህፈት ቤቱ ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ በቃል ማዘዙን ጣቢያው አመልክቷል።  

Äthiopien Eröffnung Ahadu Radio
ምስል DW/Y. G. Egziabhare

የጋዜጠኛ ታምራትን እስር በተመለከተ  የአሃዱ ኤፍ ኤም ባለቤት እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ እሸቱ በላይን አነጋግረናል። በዶይቼ ቬለ (DW) አማካኝነት በሚዘጋጀው ዓመታዊው የግሎባል ሚዲያ ፎረም ላይ ለመካፈል እዚህ ቦን ከተማ የሚገኙት አቶ እሸቱን ስቱዲያችን ጋብዘናቸው ጥያቄዎች አቅርበንላቸዋል። አቶ እሸቱ የሰጡትን ምላሽ እና የዜና ዘገባውን የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።  

ዮሃንስ ገብረእግዚያብሔር 

ተስፋለም ወልደየስ

ሸዋዬ ለገሰ