በርሊን የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የ2012 ዘገባ | ዓለም | DW | 05.12.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ዓለም

በርሊን የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የ2012 ዘገባ

መንግሥታት ሙስናን ለመከላከል ቅድሚያ ትኩረት እንዲሰጡ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ ። በተለያዩ ሃገሮች ሙስና የሚገኝበትን ደረጃ የሚገመግመው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው አመታዊ ዘገባ የመንግሥት ወጪዎች ና መንግሥት የሚሰጣቸው ውሎች

ይበልጥ ግልጽ እንዲሆኑ ጠይቋል ። ተቋሙ በአለም ዙሪያ ሙስና እየተስፋፋ መሄዱን ባሳወቀበት ዘገባው የመንግሥት ተቋማት አሠራር ተጠያቂነትን ግምት ውስጥ ያስገባ እንዲሆንም አሳስቧል ።መቀመጫውን በርሊን ጀርመን ባደረገው በተቋሙ ዘገባ መሠረት ፍተሻ ካካሄደባቸው 176 ሃገሮች በሁለት ሶስተኛው ሙስና በጣም ተስፋፍቷል ። ተቋሙ ባወጣው መዘርዘር አፍጋኒስታን ሰሜን ኮሪያ ና ሶማሊያ ሙስና በእጅጉ የተንሰራፋባቸው የመጨረሻዎቹ 3 ሃገሮች ናቸው ። በአንፃሩ ዴንማርክ ፊንላንድ እና ኒውዚላንድ እንደ አምናው በተቋሙ መዘርዝር 90 በመቶ ነጥብ በማግኘት ከሙስና የፀዱ ሊያስብል የሚያስችለውን የመጀመሪያውን ደረጃ ይዘዋል ።

Symbolbild Korruption Bestechung NO-FLASH

እንደ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ምንም እንኳን ባለፈው አመት በሙስና በተዘፈቁ መንግሥታት ላይ የተነሳው ተቃውሞ አንዳንድ መሪዎችን ከሥልጣን ቢያወርድም አሁንም በብዙ ሃገሮች ጉቦ ፣ ሥልጣንን አለአግባብ መጠቀም እና በስውር መደራደር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ። ከአረቡ አለም ህዝባዊ አብዮት በኋላ ግብፅን በመሳሰሉ ሃገሮች ሙስና እምብዛም ቀንሶ አልተገኘም ። ከዪሮ ተጠቃሚ ሃገሮችም እንደ ግሪክ ባሉት በዩሮ ቀውስ በተመቱ ሃገሮች ሙስና ተባብሷል ። በመዘርዝሩ ግሪክ አምና ከተሰጣት ደረጃ 80 ኛ አሽቆልቁላ ዘንድሮ ወደ 94 ወርዳለች ። ኢትዮጵያ 113 ኛ ኤርትራ ደግሞ 150 ኛ ደረጃ ሲሰጣቸው ፣ ቻይና 80 ኛ አሜሪካን 19 ነኛ ጀርመን ደግሞ 13 ተኛ ደረጃ አግኝተዋል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ

 • ቀን 05.12.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16wLC
 • ቀን 05.12.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16wLC