በርሊናለና የኢትዮጽያ ሲኒማ | ባህል | DW | 25.02.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

በርሊናለና የኢትዮጽያ ሲኒማ

ለአስር ቀናት የዘለቀዉ የበርሊኑ አለም አቀፍ የሲኒማ ትዕይንት ከአለም ዙርያ ለዉድድር የቀረቡ አራት መቶ ፊልም መካከል አሸናፊን በመምረጥ ባለፈዉ እሁድ ምሽት በደማቅ ዝግጅት ተጠናቆአል።

default

በርሊናለና የኢትዮጽያ ሲኒማ

በርሊና የተሰኝዉ የጀርመኑ አለም አቀፉ የፊልም መድረክ በተለያዪ የአለም አገራት የተሰሩ ፊልሞችን ብቻ ሳይሆን ለዉድድር ያቀረበዉ የፊልም ተዋናዮችን የፊልም ስራ አዋቂዎችን እና ደራሲዎችንም በዉድድሩ አሳትፎአል። የጀርመን የፊልም መድረክ በርሊናለ በታሪክ ለመጀመርያ ግዜ ሽልማቱን ለኢራኑ ፊልም ስራም አበርክቶአል። በሌላ በኩል የፊልም ዉድድር መድረኩ የፊልም ስራ እድገትን ለማሻሻል የሚረዳ የባህል የእዉቀት ልዉዉጥ መድረክም ሆኖ ነዉ የሰነበተዉ። በርሊናለ የሲኒማ ትዕይንት ላይ በጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካኝነት ተጋብዘዉ የተገኙ ኢትዮጽያዊ የፊልም ስራ አዋቂንም አስተናግዶአል። በለቱ ጥንቅራችን የጀርመኑን የአለም አቀፍ ዉድድር አሸናፊን በጥቂቱ በመቃኘት በዝግጅቱ ላይ የተገኙትን በኢትዮጽያ የብሉናይል የፊልም እና የቴሌቭዥን አካዳሚ ዋና ስራ አስኪያጅን የጀርመኑ አለም አቀፍ የሲኒማ መድረክ ለኢትዮጽያ ፊልም ስራ እድገት ያለዉን አስተዋጽ እንዲያጫዉቱን ጋብዘናል። ሙሉዉን ዝግጅት ያድምጡ!


አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ