በራሽያ የዘር ልዩነት ችግር | የጋዜጦች አምድ | DW | 07.09.2006
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

በራሽያ የዘር ልዩነት ችግር

ከታላቁዋ ሶብየት ህብረት መፈረካከስ በኻላ ሩስያ በሚኖሩ የዉጭ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመዉ በደል እና ግፍ እየተበራከተ ነዉ።

ዘረኞቹ የሚለዩበት መጫምያ

ዘረኞቹ የሚለዩበት መጫምያ

አለም አቀፉ የሰባዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት Amnesty International በቅርቡ የሩስያ ሰላም አስከባሪ ፖሊሶች ላይም ይህ የቀለም ልዩነት አድሎ ተንሰራፍቶ ይገኛል ይላል። በሩስያ የሚገኙት ወታደሮች አፍሪቃዉያኑን ከNazi ወይም ከጋጠወጦቹ የዘር ልዩነት አክራሪዎች ከሚያድኛቸዉ ይልቅ ገንዘብ መዝረፉን ተያይዘዉታል። ኢትዮጽያዉያንም አልቀረላቸዉም! በሩስያ ይህ የዘር ልዩነት ችግር ምን ያህል ችግር እያመጣ ነዉ? ምን ያህል ኢትዮጽያዉያንስ ይኖራሉ? ለከፍተኛ ትምህርት እድል የሚመጡ ተማሪዎችስ አሉ ወይ ስንል ? ከሞስኮ የኢትዮጽያን ኤንባሲን በሳንት ፒተስበርግ ነዋሪ የሆኑትን አቶ ሰለሞን ታምሩን አነጋግረናል።
አዜብ ታደሰ...
በሩስያ አለ የሚባለዉ የዘር ልዩነት ችግር ምን ያህል እዉነትን ነዉ ?
በሞስኮ በኢትዮጽያ ኤንባሲ አማካሪ አቶ ግርማ ሃይሉ «ይህ የዘር ችግር በራሽያ በተለያየ ምክንያትጥተዉ የሚኖሩ አፍሪካዉያን እንዲሁም የእስያ ዜጎች ላይ የሚደርስ ችግር አለ። በራሽያ በመንግስት በኩል ይህን ሁኔታ ለመቆጣጠር የሚደረገዉ ጥረት እንዳለ ሆኖ ችግሩ ይታያል»
በሩስያ ባጠቃላይ የቀድሞዋን ሶብየት ህብረት ጨምሮ ስንት ኢትዮጽያዉያን ይገኛሉ?
በአሁኑ ወቅት በሩስያ ፊደሪሽን እና በ CIS አገሮች በሚባሉት በጠቅላላይ የሚኖሩ ኢትዮጽያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጽያዉያን 511 በኤንባሲዉ ተመዝግበዉ ይገኛሉ። ከዚህ ዉጭ ግን በተለያየ ምክንያት እና ሁኔታ መጥተዉ የሚኖሩ ተጨማሪ ኢትዪጽያዉያን ሊኖሩ እንደሚችሉ አያይዘዉ ጠቅሰዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጽያዉያን ለትምህርት ወደ ሩስያ ፊደሪሽን ይመጣሉን?
አዎ! በአሁኑ ወቅት በሩስያ ፊደሪሽን በሁለት መልኩ የመጡ ኢትዮጽያዉያን ተማሪዎች አሉ። 13 የሚሆኑት በትምህርት ሚ/ር በኩል ለከፍተኛ ትምህርት ማለትም የ PHD ዲግሪያቸዉን ሊያጠኑ የመጡ ከፍተኛ የትምህርት መምህራን አሉ። ከዚህ ዉጭ በቅድመ ምረቃ ትምህርት በሩስያ ዉስጥ በመንግስትም ሆነ በግል ዩንቨርስቲዎች ዉስጥ እየተከታተሉ ያሉ ከ 70 የሚበልጡ ኢትዮጽያዉያን ተማሪዎች አሉ።
የዘር ልዩነትን ለመቃወም በሩስያ የሚገኙ የአፍሪቃ አገር አንባሳደሮች ለመንግስት ምን ያህል ቅሪታቸዉን እንዳሰሙ ለተጠየቁት «በሩስያ ፊደሪሽን ዉስጥ የሚገኙ የአፍሪቃዉያን አንባሰዳሮች ቡድን ተቋቁሞአል፣ ቡድኑ በጋራ በየወሩ በመሰብሰብ የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ይወያያል። አንዱ የጋራ ችግራችን ይህ የራሲዝም ወይም የዘር አድሎ ችግርን በመሆኑ ችግሩ ባይፈታም በተለያየ ግዜ ችግሩን አሳዉቀናል። በሞስኮ እና አካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጽያዉያን ማህበርም በማቋቋም በተለይ ኢትዮጽያዉያን ላይ የሚደርሱ ችግሮችን ኤንባሲዉ ከማህበሩ ጋር በመተባበር ችግሩን ለመፍታት ጥረት ያደርጋል። ይህ የኢትዮጽያዉያን ማህበር ጠብካራ ነዉ ብሎ መናገር ይቻላል»ባይ ናቸዉ።
የሩሲያን እንግዳ ተቀባይነት የማይታበል ሃቅ ቢሆንም፣ በሩስያ አንዳንድ ጋጠወጥ ወጣቶች በርካታ አስከፊ ሁኔታን፣ በተለይ በአፍሪቃዉያን ላይ ሲፈጽሙ ይታያል። ስለዚህ ጉዳይ ኢትዮጽያዉያን ምን ይላሉ? ከሳንት ፒተርስበርግ በቀድሞዋ (ሌሊን ግራድ) ነዋሪ አቶ ሰለሞን ታምሩ በመጀመርያ በምን ምክንያት ወደ ራሽያ እንደሄዱ ሲገልጹ «የመጣሁት እ.አ 1988 ዓ.ም በዉትድርና ትምህርት በቀድሞ የኢትዮጽያ አየር ሃይል በኩል ተልኬ ነበር። በርግጥ ትምህርቴን ከጨረስኩ ቆይቻለሁ ማለትም እ.አ 1993 ዓ.ም ነበር። ነገርግን በራሴ ችግር ምክንያት ወደ አገሬ መመለስ አልፈለኩም፣ አልቻልኩም። ከዚያ ቤተሰብ መስርቼና በንግድ ስራ ተሰማርቼ ኑሮዪን እዚህ አድርጌአለሁ። የዘር ልዩነት በሩስያ በጣም ተስፋፍቶ ይገኛል። እንዲህ አይነቱ ችግር መከሰት የጀመረዉ እ.አ 1990 ዎቹ መጀመርያ ላይ ነዉ። በቀድሞዋ ሶብየት ህብረት ድሮ እኛ አዲስ ተማሪዎች እያለን የነበረዉ የሰዉ ፍቅር እና ለዉጭ አገር ዜጎች ያለዉ ክብር ጠፍቶ በተለይ በዚህ 3 - 4 አመታት አስቀያሚ የሆነ ነገር መከሰት ጀምሮአል። እንደሚታወቀዉ በሁለተኛዉ አለም ጦርነት በ U.S.S.R ከሁሉም አገሮች የበለጠ ብዙ ሚሊዮን ህዝብ መስዋት ሆንዋል። የጦርነቱ ተካፋይ የነበሩ አርበኞች የልጅ ልጆች፣ ዛሪ እነዚህ አርበኞች በህይወት እያሉ የናዚን አርማ አንግበዉ፣ ሰንደቃላማዉን ተሸክመዉ በከተማ ወስጥ ሲንሸራሰሩ እና ሰልፍ ሲወጡ ማየቱ በጣም ያሳዝናል። ከዚህ በመቀጠል የዉጭ አገር ዜጎችን በመንቀፍ ራሽያ ለራሽያኖች ብቻ! በማለት የዉጭ ዜጎችን በመደብደብ ከዚያም የተማሪዎች መኖርያ ድረስ በመምጣት የአካል ጉዳት በማድረስ ብዙ አሰቃቂ ነገሮች ሲደረጉ ቆይተዋል። በመጨረሻዎቹ አምስት አመታት ግን የዉጭ አገር ዜጎችን መደብደብ ሳይሆን መግደል ጀምረዋል። ጠዋት ወጥቶ ማታ ለመግባት አስጊ የሆነበት ወቅት ነዉ! ባለፈዉ መጨረሻ ወር ትንሽ ጋብ ያለ ይመስላል። ምክንያቱም በቅርቡ በሳንት ፒተርበርግ የስምንቱ ታላላቅ አገር መሪዎች ስብሰባ በነበረበት ወቅት አንዳንድ አመቺ ያልሆኑ ሰዎችን መንግስት ሰብስቦ አስሮአል። ታድያ ነገሩ ጠፋ ማለት ሳይሆን ለግዜዉ ጋብ ብሎአል»የራሽያ ፊደሪሽን ኑሮ ይህን ይመስላል