በሪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ተሳትፎ እና ውጤት | ስፖርት | DW | 17.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ስፖርት

በሪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ተሳትፎ እና ውጤት

በቀሪዎቹ ውድድሮች ተጨማሪ ሜዳልያዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።13 ተኛ ቀኑን በያዘው የሪዮ ኦሎምፒክ የሜዳልያ ሰንጠረዥ ኢትዮጵያ ዛሬ 40 ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:54

በርዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ አትሌቶች ተሳትፎ እና ውጤት

በሪዮ ኦሊምፒክ ትናንት ሌሊት በተካሄደው 1,500 ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳልያ አግኝታለች ገንዘቤ ወደፊት 1,500 ሜትር ሩጫ የመወዳደር እቅድ እንደሌላት ተናግራ 5,000 ሜትር ሩጫ ግን ክብረ ወሰኑን ለመስበር ግን ሙከራ እንደምታደርግ አስታውቃለች በዛሬው ዕለት በሁለት ምድብ በተካሄደው 5,000 ሜትር የወንዶች ሩጫ የማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ደጀን ገብረመሥቀል፣ ሐጎስ ገብረሕይወት እና ሙክታር ኢድሪስ አልፈዋል ። የፍፃሜው ውድድሩ የፊታችን ቅዳሜ ይደረጋል።ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሚቀጥሉት ቀናት የሚሳተፉባቸው ቀሪ ውድድሮች አሉ ። በነዚህ ውድድሮችም ተጨማሪ ሜዳልያዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ከውድድሮቹ ምን ይጠበቃል በእስካሁኑ ውድድር የተገኙት ውጤቶችስ እንዴት ይታያሉ?የለንደንዋን ዘጋቢያችንን ሃና ደምሴን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬያታለሁ ።

ሃና ደምሴ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic