በሩር አዉራጃ የአዉራ ጎዳና ድግስ | ባህል | DW | 22.07.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

በሩር አዉራጃ የአዉራ ጎዳና ድግስ

እዚህ በጀርመን የአዉሮጻዉያኑ 2010 አ.ም የባህል ማዕከል በተሰኘዉ በሩር አዉራጃ በሚገኘዉ ስድሳ ኪሎ ሜትር አዉራ ጎዳና ላይ ስለተደረገዉ የደግስ ፈንጠዝያ እንዲሁም አንዲት በቅርቡ ወደ ጀርመን የመጣች የባህል መዚቃ መሳርያ ተጫዋች በቅንብሩ ይዞአል ለቅንብሩ አዜብ ታደሰ ነኝ መልካም ቆይታ

default

በያዝነዉ የአዉሮጻዉያን አዲስ አመት በጀርመን ትልቅ ግዛት እንደሆነ በሚታወቀዉ እዚህ በኖርዝ ራይን ዊስት ፋልያ ግዛት በሚገኘዉ የሩር አካባቢ የአዉሮጻ የባህል ማዕከል በመሆን መመረጡን መግለጻችን የሚታወስ ነዉ። አካባቢዉ በሚገኘዉ የሩር ወንዝን ስያሜ ይዞ ያለዉ አካባቢ አምስት ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርበት ሲሆን በጀርመን ዉስጥ ካሉ አካባቢዎች ሁሉ በርካታ ህዝብን አቅፎ በመያዙ አንደኛ ከአዉሮጻ አገሮች ደግሞ ሶስተኛ በመሆኑ ይታወቃል። የሩር አካባቢ በርካታ ኢንዱስትሪን አቅፎ የያዘ በተለይም የድንጋይ ከሰል የሚወጣበት ቦታ በመሆኑ ነበር በርካታ ነዋሪዎች በአካባቢዉ ሰፍረዉ የሚኖሩት። የከሰል ድንጋይ ተፈላጊነቱ እየቀነሰ ሲሄድ በዛዉ አካባቢ ያሉ ህዝቦች አካባቢያቸዉን በመቀየር በፋብሪካዉ ምትክ የጸሃይ ወይም የነፋስ ሃይል ምንጭ መሰብሰብያ በመትከል የመሪቱን ለምነት በመጠበቅ ቦታዉ ልዩ መስብ እንዲኖረዉ አድርገዉታል።

በ 1950 ዎቹ በጀርመን የታየዉን ከፍተኛ የኢኮነሚ እድገት መሰረት የሆነዉ ይኸዉ የሩር አዉራጃ ማለት Ruhrgebiet የነበረዉን የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ የሚያመርተዉ ምርት በአለም ገበያ ፈለጊነቱ እየቀነሰ በመምጣቱ ይህንን ግዙፍ እንዱስትሪ ለማፍረስ ደግሞ የአመታት ግዜን ጠይቋል።

በዶርትሙንድ ከተማ አቅራብያ ሰላሳ የእግር ኳስ መጫወቻ ቦታን የሚያህል ክልል ላይ በቀድሞ የከሰል ድንጋይ ማዉጫ የነበረዉ ቦታ ከአዉሮጻዉያኑ 2001 አ.ም ጀምሮ ታጥሮ ምንም ሳይሰራበት የቆመ ነበር። በአሁኑ ወቅት ግን በዚህ ትልቅ ክልል ላይ ሸለቆ ቦታዎችን በመድፈን እና በማስተካከል ሰዉ ሰራሽ ባህር፤ የተለያዩ መስዕቦችን እና መዝናኛዎችን ለመስራት የሚደረገዉ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ ስራዉ ተጀምሮአል። ይህ ቦታ ታድያ በህብረተሰቡ ዘንድ ዳግም ታዋቂ እንዲሆን ቦታዉ የቱሪስት መስዕብ እንዲኖረዉ ጥረት በመደረግ ላይ ነዉ። ባለፈዉ ሳምንት እሁድ አዉራጃዉ ዉስጥ ያለዉ ስድሳ ኪሎሜትር የፈጣን

Still-Leben A40 Flash-Galerie 026

ተሽከርካሪ መንቀሳቀሻ አዉራ ጎዳና ላይ ሶስት ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ የጎዳና ላይ ፈንጠዝያ እና ድግስ ሲያደርግ ዉሎአል።
የጀርመን አዉራ ጎዳና በሰአት ቢያንስ ከሰማንያ እስከ መቶ ሰባ ሰማንያ መኪና የሚበርባቸዉ የሚበርበት ሲሆን A40 የተሰኘዉ በሩር አዉራጃ የሚገኘዉ አዉራ ጎዳና «በጸጥታ ኑሮ» በተሰኝ መርሆ ስድሳ ኪሎሜትር አዉራ ጎዳና ላይ መኪና ሳይኖር ጠረቤዛ ተዘርግቶ፣ በብስክሌት እና በእግር በመጓዝ እና በመደነስ የሩር አዉራጃ መዝናኛ ቦታዎችን በማስተዋወቅ በመብላት በመጠጣት እለቱ ተከብሮአል።

እንደ ጀርመን የትራንስፖርት ሚኒስቴር ዘገባ በዚህ አዉራ ጎዳና ላይ በአንድ ቀን ብቻ 100,000 መኪናዎች ይመላለሳሉ። በእዚህ እለት ግን መኪናዉ ቀርቶ ሃያ ሽህ ረዣዥም ጠረቤዛዎች ተዘርግተዉ ምግብ መጠጥ ቀርቦ ለድግሱ የመጣዉን እግር መንገደኛም ሆነ ብስክሌት አሽከርካሪ ሲያዝናኑ ዉለዋል። ከእድምተኛዉ አንዱ እንደገለጹት «ባህል ማለት ለኔ፣ ጥበብ ብቻ ሳይሆን የህዝብ አኗኗር እና የስራ አይነትም ነዉ። እናም የህዝብ አኗኗር የሚተገብረዉ ስራ እና የትዉልድ ቦታዉን ሁሉ ያጠቃልላል»

በሁለተኛነት የያዝነዉ ርዕስ በአንዲት ወጣት ከያኒ ዙርያ ያቆየናል። ማርታ ተፈራ ትባላለች የጀርመን መዲና ነዋሪ የሆነችዉ በቅርቡ ነዉ። ከአገሪ ስወጣ ምን ግዜም ቢሆን ክራሪን ይዤ ነዉ ስትል ገልጻልናለች! ባቲ አንቺ ሆዪ ትዝታና እና አንባሰልን ተጫዉታልናለች ያድምጡ!


አዜብ ታደሰ
ሸዋዪ ለገሰ

ተዛማጅ ዘገባዎች