በረሃብ ለተጎዱት ለየመንና ለአምስት የአፍሪቃ ሃገራት ርዳታ  | ዓለም | DW | 27.03.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

በረሃብ ለተጎዱት ለየመንና ለአምስት የአፍሪቃ ሃገራት ርዳታ 

የዓለም ባንክ ለየመንና ለሌሎች አምስት የአፍሪቃ ሃገራት የሚዉል የ 1.6 ቢሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ርዳታ እንደሚሰጥ አስታወቀ። የርዳታ ገንዘቡ ለሶማልያ ለደቡብ ሱዳን ፤ ለኬንያ ለኢትዮጵያ፣ ለናይጀርያና በየመን ለሚገኙ በድርቅ ለተጎዱ ነዋሪዎች የሚዉል እንደሆነ ተገልጿል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:02

ከዓለም ባንክ የ 1.6 ቢሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ርዳታ


የዋሽንግተኑ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ያነጋገራቸዉ የኢኮኖሚ ጉዳይ ምሁር እንደገለጹት ርዳታዉ ጊዜያዊ እንጂ ለዘለቄታ የሚያመጣዉ መፍትሄ እንደሌለ ተናግረዋል። ድርቁም ሰዉ ሠራሽና ከሰላምና መረጋጋት እንደሚያያዝ በየትኛዉም የዓለም ክፍል የሚታይ እዉነታ መሆኑንም አመልክተዋል። 
መክብብ ሸዋ 


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ 

Audios and videos on the topic