በሞሮኮ ይደረጋል የሚባለው ተሀድሶ | ኢትዮጵያ | DW | 12.03.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በሞሮኮ ይደረጋል የሚባለው ተሀድሶ

የሞሮኮ ንጉስ መሀመድ ሳድሳይ በሀገራቸው የፖለቲካ ተሀድሶ ሊያደርጉ ነው።

default


በሰሜን አፍሪቃ እና በሌሎች ዐረባውያት ሀገሮች የተጀመረውን የህዝብ ዓመጽ ተከትሎ የሞሮኮ ህዝብም በሀገሩ ዴሞክራሲያዊው ስርዓት እንዲተከል ካለፉት ሶስት ሳምንታት ገደማ ወዲህ አደባባይ በመውጣት ሲጠይቅ መሰንበቱ የሚታወስ ነው። የህዝባቸውን ጥያቄ ከግንዛቤ ያስገቡት የሀገሪቱ ንጉስ መሀመድ ሳድሳይ ሰፊ የህገ መንግስት ማሻሻያ ለውጥ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ንጉሱ ከሁለት ቀናት በፊት ለሀገራቸው ህዝብ ባሰሙት ንግግር ይፋ እንዳደረጉት፡ የተያዘው አውሮጳው ዓመት 2011 ሳያበቃ በፊት በአዲስ ህገ መንግስት ላይ ህዝበ ውሳኔ ይካሄዳል።

አርያም ተክሌ