1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በምዕራብ ጎጃም ዞን የቀጠለው ውግያ

ቅዳሜ፣ መስከረም 25 2017

በፍኖተ ሰላም ከተማ ትናንት ውጊያ እንደነበር የነገሩን አንድ የከተማዋ ነዋሪ ዛሬ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በከተማው ማረሚያ ቤት በተባለው አካባቢ ሲንቀሳቀሱ ማየታቸውንም አመልክተዋል። ይሁን እንጂ በጅጋ መስመር “ሆድ አንሺ” አካባቢ የተኩስ ልውውጦች እንደሚሰሙም አክለዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4lRWm
Äthiopien Landschaft Brücke am Abay-Fluss
ምስል Seyoum Getu/DW

በምዕራብ ጎጃም ዞን የቀጠለው ውግያ

በአማራ ክልል በተለይም በምዕራብ ጎጃም ዞን አንዳንድ አካባቢዎች ካለፉት 2 ቀናት ጀምሮ ውጊያዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄዱ እንደሆነ የየከተሞቹ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።በአንዳንዶቹ አካባቢዎች ውጊያው በረድ ሲል፣ በፍኖተ ሰላምና  ጂጋ ከተሞች መካከል ላይ በምትገኘው “ሆድ አንሺ” በተባለች ቀበሌና በደንበጫ ከተማ ውጊያው ቀጥሎ መዋሉን አስተያየት ሰጪዎች አመልክተዋል፡፡

ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ በምዕራብ ጎጃም ዞን ጂጋ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ደንበጫና ቡሬ ከተሞችና ዙሪያው በመንግስት የፀጥታ ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከልከባድ ውጊዎችእንደነበሩ ነዋሪዎች ለዶቼ ቬሌ በስልክ ተናግረዋል፡፡

ጅጋ በተባለችው አነስተኛ ከተማ ትናንት ከባድ ውጊያ እንደነበር የነገሩን እንድ የከተማዋ ነዋሪ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ዛሬ እስከ ቀኑ 7 ሰዓት ድረስ በከተማዋ የፋኖ ኃይሎች ይንቀሳቀሱ እንደነበር ጠቅሰው ሆኖም “በፍኖተ ሰላምና  ጂጋ ከተሞች መካከል ላይ በምትገኘው “ሆድ አንሺ” በተባለች ቀበሌ የከባድ መሳሪያ ድምፅ አሁንም ይሰማል” ብለዋል፡፡

በፍኖተ ሰላም ከተማ ትናንት ውጊያ እንደነበር የነገሩን አንድ  የከተማዋ ነዋሪ ዛሬ በአንፃሩ የተኩስ ድምፅ በከተማዋ አይሰማምም ብለዋል። የመንግስት የፀጥታ ኃይሎችን በከተማው ማረሚያ ቤት በተባለው አካባቢ ሲንቀሳቀሱ ማየታቸውንም አመልክተዋል። ይሁን እንጂ በጅጋ መስመር “ሆድ አንሺ” አካባቢ ውጊያ መኖሩን የሚያረጋግጡ የተኩስ ልውውጦች እንደሚሰሙ ነው ያብራሩት፡፡

በዚሁ በምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫ ከተማ ከትናንትና ጀምሮ ውጊያው በሁለቱ ኃይሎች መካከል እንደቀጠለ መሆኑን ደግሞ የከተማዋ ነዋሪ ዛሬ ቀትር ላይ ነግረውናል፡፡ ሰው ከቤት እንደማወጣና የሚሆነውን ቁጭ ብሎ እየጠበቀ እንደሆነ ተናግረዋል፣ ይህን ቃለመጠይቅ በሚሰጡበት ጊዜ ከባድ ተኩስ ድምፅ እየተሰማ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ትናንት በዙሪያዋ የተኩስ ድምፅ ሲሰማባት የዋለችው የቡሬ ከተማ ዛሬ አንፃራዊ መረጋጋት እንዳለባት አንድ የከተማዋ ነዋሪ ለዶይቼ ቬሌ ገልጠዋል። ትናንት በተኩስ ልውውጥ የሞቱ የሁለት ሰዎች ቀብር መከናወኑንም ገልጠዋል፡፡፡፡

የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መንገሻ ፋንታውና የመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ሰሞኑን በጋራ ለመንግስት መገናኛ ብዙሐን በሰጡት መግለጫ በአማራ ክልል “ዘላቂ ሰላም ለማስፈን” ያሉት ህግ የማስከበር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው ነበር፡፡

ዓለምነው መኮንን

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር