በምዕራብ ኦሮሚያ ፈታኝ ሆኖ የቀጠለው የፀጥታ ችግር | ኢትዮጵያ | DW | 08.03.2022
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በምዕራብ ኦሮሚያ ፈታኝ ሆኖ የቀጠለው የፀጥታ ችግር

በኦሮሚያ ክልል ከተለያዩ ዞኖች ተፈናቅለው በሰው ቤት እና በመጠለያዎች የሚገኙ ዜጎች አስቸጋሪ ያሉት የደህንነትና የኢኮኖሚ ችግር ውስጥ መውደቃቸውን አመለከቱ፡፡ በክልሉ የጸጥታ ችግር ባጋጠመባቸው አከባቢዎች የትራንስፖርት እና የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፈተና ውስጥ በመሆናቸው አስከፊ ያሉት ሁኔ ውስጥ እያሳለፉ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:33

ህብረተሰቡ በፀጥታ ስጋት ውስጥ ነዉ እየኖረ የሚገኘዉ

በኦሮሚያ ክልል ከተለያዩ ዞኖች ተፈናቅለው በሰው ቤት እና በመጠለያዎች የሚገኙ ዜጎች አስቸጋሪ ያሉት የደህንነትና የኢኮኖሚ ችግር ውስጥ መውደቃቸውን አመለከቱ፡፡
በክልሉ የጸጥታ ችግር ባጋጠመባቸው አከባቢዎች የትራንስፖርት እና የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፈተና ውስጥ በመሆናቸው አስከፊ ያሉት ሁኔ ውስጥ እያሳለፉ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ መንግስት በበኩሉ የክልሉ ሰላም ያደፈርሳሉ ባላቸው የታጣቂ ኃይላት ላይ የሚወስደውን ርምጃ ማጠናከሩን ነው የሚገልጸው፡፡
አንድ ከምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ስሬ ወረዳ በታጣቂዎች ይደርስብናል ያሉትን ጥቃት ሸሽተው በምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮ ከተማ ከዘመድ ቤት ተጠልለው እንደሚገኙ የሚገልጹት ተፈናቃይ ማኅበረሰቡ ለተለያዩ ችግሮች እንደሚዳረግ ነው የሚገልጹት፡፡ ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁን እኚህ ተፈናቃይ፤ በብዛት ብሔር ላይ አነጣጥሮ ይፈጸማል ባሉት የታጣቂዎች ጥቃት በየወረዳው ከተሞች የተፈናቃዮች ካምፕ ቢዘጋጅም ኅብረተሰቡ ሁሌም በፀጥታ ስጋት ውስጥ እንደሚኖሩ አብራርተዋልም፡፡  
በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ሌላው ሰው በሰጡን አስተያየት እንዳመለከቱት፤ ያለ ብሔር ገድብ በመላው ማኅበረሰብ ላይ ደርሷል ባሉት የፀጥታ ችግር ወደ አቅራቢያ ከተሞች እና መዲናዋ አዲስ አበባ የሚወስዱ መንገዶች በመዘጋታቸው ተሽከርካሪዎች አይንቀሳቀሱም፡፡ ይህ ደግሞ እንዳማራጭ ሌላ እጥፍ ርቀት የሚወስደውን መንገድ ለመጠቀም ከማስገደዱም  ባለፈ በመሰረታዊ ፍጆታ እቃ እጥረት ለኑሮ ውድነትና ለህይትም ፈታኝ ሁኔታ መዳረጋቸውን ነው የሚገልጹት፡፡  
ከሆሮ ጉዱሩ ዞን ጃርደጋ ጃርቴ ተፈናቅለው አሁን ላይ በደቡብ ወሎ በተፈናቃዮች መጠለያ መሆናቸው የሚገልጹት ሌላው ተፈናቃይም በአከባቢው ካለው የፀጥታ ሁኔታ ማምለጥ ያልቻሉት እየተጋፈጡት ነው ያሉትን የህይወት ብርቱ ፈተና እንዲህ አጋርተውናል፡፡ አፕ….
ስለ ክልሉ አሁናዊ የፀጥታ ተግዳሮቶች እና እየተወሰደ ሲለሚገኘው የመፍትሄ ርምጃ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን እና ከኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ለመጠየቅ ያደረግነው ሙከሪያ ለጊዜው አልተሳካም፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት በይፋዊ የማኅበራዊ ገጹ ላይ በሰጠው መረጃ እንዳመለከተው ግን የፀጥታ ኃይሎቹ ከፌዴራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ጠላት ያለው ታጣቂ ቡድን ላይ የኃይል እየወሰደ መሆኑን አመልክቷል፡፡ 
መንግስት ለኅብረተሰቡ እሮሮ ስላስቀመጠው ምላሽ እና የመፍትሄ አቅጣጫ የተጠየቁት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ እንደመለሱትም፤ በክልሉ በዋናነት ለሚደፈርሰው ሰላም ሸኔ ያሉት የኦሮሞ ነጻነት ጦርን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡ 


ሥዩም ጌቱ 


አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ 
 

Audios and videos on the topic