በምስራቅ ወለጋ የቀጠለዉ የታጣቂዎች ጥቃት | ኢትዮጵያ | DW | 24.01.2022
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በምስራቅ ወለጋ የቀጠለዉ የታጣቂዎች ጥቃት

በምስራቅ ወለጋ 6 ሰዎች ትናንት መታገታቸውን እና የጸጥታ ኃይሎች ለማስለቀቅ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ነው፡፡ በምስራቅ ወለጋ ስቡ ስሬና ጎቡ ሳዩ በሚባሉ ወረዳዎች መካከል ሰዎች መታገታቸውን የዞኑ አስተዳደር አረጋግጠዋል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:23

በምስራቅ ወለጋ ስቡ ስሬና ጎቡ ሳዩ በሚባሉ ወረዳዎች

በምስራቅ ወለጋ 6 ሰዎች ትናንት መታገታቸውን እና የጸጥታ ኃይሎች ለማስለቀቅ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ነው፡፡ በምስራቅ ወለጋ ስቡ ስሬና ጎቡ ሳዩ በሚባሉ ወረዳዎች መካከል ሰዎች መታገታቸውን የዞኑ አስተዳደር አረጋግጠዋል፡፡ የምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ተስፋ  ትናንት ታገቱ ስለተባሉ ሰዎች እያጣሩ እንደሚገኙ ለዲዳቢሊው ተናግረዋል፡፡ በስፋራው ሰዎችን ያገቱት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱት የሸነ ቡድን እንደሆኑም አክለዋል፡፡

የምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ተስፋ  በዞናቸው የተለያዩ ስፍራዎች በተለይም የጸጥታ ሀይሎች በቶሎ በማይደረሱባቸው አካባቢዎች የታጠቁ ሸማቂ ሀይሎች ሰዎችን እንደሚያግቱ ለዲዳቢሊው ተናግረዋል፡፡ መንግስት በአሸባሪነት የፈረጀው ሸኔ ቡድን ዜጎችን በማገት እና በማፈናቀል ንብረትም ይዘርፋል ብለዋል፡፡ በትናትናው ዕለትም በዞኑ ስቡ ስሬና ጎቡ ሰዩ በተባሉ ወረዳዎች መካከል  ሰዎች መታገታቸው እና የጸጥታ ሀይሎች ጉዳዩን ለማጣራት እና የታገቱ ዜጎችን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡ በዞናቸው ሸማቂዎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ቤተሰቦችን በማገት እና ገንዘብ በመጠየቅ እንደሚያንገላቱም አብራርተዋል፡፡

በዞኑ ስር ከሚገኙት 18 በሚደርሱት ወረዳዎች መካከል አምስት በሚደርሱት ወረዳዎች ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት በደረሱት ጥቃቶች ለተፈናቀሉ ዜጎችም ሰብአዊ እርዳት የማዳረስ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለማየው ተስፋ ተናግረዋል፡፡ በዞኑ ኪራሙ፣ዲጋ፣ ስቡ ስረ፣ ጉቱ ግዲና ሌሎችም ስፋራዎች በርካታ ሰዎች የተፈናቀሉበት ወረዳዎች መሆናቸውን ከዚህ ቀደም በሰጡን ማብራሪያም አመልክቷል፡፡

ከምስራቅ ወለጋ  ዞን ከተማ ነቀምቴ በ50 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚትገኘው ስቡ ስሬ ወረዳ በታጣቂዎች ከዚህ ቀደም በደረሰው ጉዳት ዜጎች ተፈናቅለው እንደነበርም  አንድ የወረዳው ነዋሪ ገልጸዋል፡፡ በትናንትው ዕለት 10፡00 ገደማ ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ ሲጓዙ የነበሩ 6 ዜጎች በምስራቅ ወለጋ ጎቡ ሰዩ ወረዳ ውስጥ መታገታቸውን የፌደራል የደህንነትና ጸጥታ የጋራ ግብረ ሀይል ማስታወቁን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን ዘግቧል፡፡ ከታገተቱት መካከልም አምስት ተማሪዎች እና አንድ በንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ሰው መሆኑንም ተመላክቷል፡፡

 

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች