1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምስራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ ታጣቂዎች 17 ሰላማዊ ሰዎች መግደላቸው

ቅዳሜ፣ መስከረም 8 2014

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ትናንት በስትያ ሐሙስ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አሥራ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለDW ተናገሩ።በጥቃቱ  ከተገደሉት በተጨማሪ ስድስት ሰዎች የገቡት አለመታወቁንም የአይን እማኞቹ ገልጸዋል ።

https://p.dw.com/p/40VQe
Äthiopien | Wahlen | Oromia

ምስራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ ታጣቂዎች 17 ሰላማዊ ሰዎች መግደላቸው ተሰማ

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ትናንት በስትያ ሐሙስ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አሥራ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለDW ተናገሩ።በጥቃቱ  ከተገደሉት በተጨማሪ ስድስት ሰዎች የገቡት አለመታወቁንም የአይን እማኞቹ ገልጸዋል ።
 በዞኑ ኪረሙ እና አሙሩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ቀበሌዎች ከመንግሥት ቁጥጥር ውጪ ሆነው በ«ኦነግ ሸኔ በታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር እንደሚገኙም ነው ነዋሪዎቹ የሚናገሩት ። በዚህም በአካባቢው የመንግስት ባለስልጣናትም ሆኑ የጸጥታ ኃይሎች ሰላማዊ ሰዎችን መከላከልበማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አስረድተዋል። 
በሰሞንኛው ጥቃትም ሆነ በአካባቢው ስላለው ተጨባች ሁኔታ ዶይጬ ቬለ ከአካባቢው እና ከክልል የሥራ ኃላፊዎች ለመጠየቅ ያደረገው  ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ