በምርጫ 2013 በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያውያን ሚና | ኢትዮጵያ | DW | 11.04.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በምርጫ 2013 በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያውያን ሚና

በምርጫ ሕጉ መሰረት በተለምዶ ዳያስፖራ በሚለው የእንግሊዘኛ ቃል የሚጠሩት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን  መምረጥም ሆነ መመረጥ ባይችሉም በተለያዩ መንገዶች አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል።

በምርጫ 2013 የዳያስፖራው ሚና

ኢትዮጵያ የፊታችን ግንቦት መጨረሻ ለምታካሂደው ምርጫ የሚደረገው ዝግጅት ቀጥሏል።በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ ነው። በየመድረኩ ከሚደረጉ የምርጫ ቅስቀሳዎች ጎን ለጎን በመገናኛ ብዙሀንም የምርጫ ዘመቻው ቀጥሏል።በኢትዮጵያ የምርጫው ዝግጅት በቀጠለበት በዚህ ወቅት ላይ በውጭ ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም ለምርጫው የበኩላቸውን መወጣታቸው አልቀረም።በውጭ ሃገራት ምርጫው ላይ ያተኮሩ ውይይቶች ይካሄዳሉ።  በምርጫ ሕጉ መሰረት በተለምዶ ዳያስፖራ በሚለው የእንግሊዘኛ ቃል የሚጠሩት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መመረጥም ሆነ መምረጥ ባይችሉም በተለያዩ መንገዶች አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል። በምርጫ 2013 በውጭ የሚኖሩ ዜጎች ሚና ምን ይሆን? ምን አስተዋጽኦስ ማድረግ ይችላሉ? ስጋቶቻቸውስ ምንድናቸው? የዛሬው እንወያይ ትኩረት ነው።በዚህ ርዕስ ላይ የሚወያዩ ሦስት እንግዶች ጋብዘናል ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆነው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ሃላፊ ፣ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ ጀርመን የሚኖሩ የኢኮኖሚ ምሁር እንዲሁም ህሊና ሙላቱ በምርጫ ጉዳዮች ላይ ውይይት የሚያዘጋጀው መቀመጫውን ቤልጀየም ያደረገው «ድልድይ የኢትዮጵያኖች መድረክ» ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የቤልጅየም ነዋሪ ናቸው።

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic