በምሥራቅ የዩክሬይን ከተማ በስሎቭያንስክ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩ | ዓለም | DW | 02.05.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

በምሥራቅ የዩክሬይን ከተማ በስሎቭያንስክ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩ

የዩክሬይን መንግሥት ወታደሮች ስሎቫንስክን ፣ መነጠል ይፈልጋሉ ከሚባሉት መፍቀሬ- ሩሲያ ኃይሎች እጅ አስለቅቆ ለመቆጣጠር ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻ መክፈታቸውን ጊዜያዊው የሀገር አስተዳደር ሚንስትር አርሰን አባኮቭ ገለጡ።

ምሥራቁ ዩክሬይን እንዲገነጠል የሚሹት ወገኖች በተጠቀሰችው ከተማ 2 ሄሊኮፕተሮች መትተው መጣላቸውንና ሁለቱም አብራሪዎች መሞታቸውን የዩክሬይን መከላከያ ሚንስቴር አስታውቋል።

የኪየቭ መንግሥት ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች ወደ ስሎቫንስክ በማምራት ላይ መሆናቸውንና ወደ ከተማይቱ ሠርገው የገቡ ወታደሮች እንዳሉ፤ በተለያዩ ጣቢያዎችም ውጊያ መከፈቱን ፤ ቭላዲስላቭ በሚል የመጀመሪያ ስም የሚጠቀሱት የመፍቀሬ ሩሲያውያኑ ወታደራዊ ክንፍ ይፋ ቃል አቀባይ አስታወቀዋል።

ተክሌ የኋላ