በምልክት ቋንቋ ስለ ኮሮና መረጃ የምታደርሰዉ ወጣት | ወጣቶች | DW | 20.03.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ወጣቶች

በምልክት ቋንቋ ስለ ኮሮና መረጃ የምታደርሰዉ ወጣት

የኮሮና ስርጭትን ለመግታት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሰማርተዉ ጊዚያቸውን፣ ጉልበታቸዉንና ገንዘባቸዉን መሰዋዓት በማድረግ የተቸገሩ ወገኖቻቸዉን በመርዳት ላይ የሚገኙም ወጣቶች ጥቂት አይደሉም። ወጣቷ ጋዜጠኛ መዓዛ መላኩ ከእነዚህ ቅንና በጎ አሳቢ ሰዎች መካከል አንዷ ናት።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:13

የምታደርሰዉ መረጃ ከታመኑ ምንጮች የተገኙ ናቸዉ

የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰቱን የጤና ጥበቃ ምንስቴር ካረጋገጠ ካለፈዉ መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም ወዲሀ በመጥፎም ይሁን በደግ የሚሰሙና የሚታዩ በርካታ ነገሮች አሉ። ቤቶቻችሁን ፀረ-ተኅዋሲ መድሐኒተ አንረጫለን በሚል የዝርፊያ ሙከራ ከሚያደርጉት ጀምሮ ወረሩሽኙን ለመከላከል ይረዳሉ የተባሉ የፊት መሸፈኛ ጭንብሎችን፣ የንጽህና መጠበቂያ ሳሙናዎቸና ኬሚካሎችን አንዲሁም የምግብና የሸቀጣ ሸቀጦችን ዋጋ በአጥፍ አስከ መጨመር የደረሱና አጋጣሚዉን ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሊጠቀሙበት የሞከሩ አልጠፉም። በአንጻሩ ደግሞ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሰማርተዉ ጊዚያቸውን፣ ጉልበታቸዉንና ገንዘባቸዉን መሰዋዓት በማድረግ የተቸገሩ ወገኖቻቸዉን በመርዳት ላይ የሚገኙም አሉ። ወጣቷ ጋዜጠኛ መዓዛ መላኩ ከእነዚህ ቅንና በጎ አሳቢ ሰዎች መካከል አንዷ ነች። መዓዛ የኮሮና ወረሩሽኝ በኢትዮጰያ ተከሰተ ከተባለበተ ጊዜ ጀምሮ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በምልክት ቋንቋ ስለ ኮሮና ቫይረስ መረጃዎችን መስማት ለተሳናቸዉ ወገኖች በማድረስ ላይ ትገኛለች። 

የመጀመሪያ ዲገሪዋነ ከአዲስ አበባ ዩነቨረሲቲ  ሁለተኛ ዲግሪዋን ደግሞ በኖርዌ አስሎ ዩንቨርሲቲ በልዩ ፍላጎት ትምህርት የተከታተለችዉና ላለፉተ 5 ዓመታትም በጋዜጠኝነት ሙያ በመስራት ላይ የምትገኘዉ መዓዛ ከመደበኛ ሰራዋ ጎን ለጎን የጀመረችዉን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ግዴታየን አየተወጣሁ ነው በላ ታሰባለች። 

የኮሮና ቫይረስ መከሰት ከታወቀብት ከጎረጎሪያኑ ያለፈዉ ታኅሳሰ ወር ጀምሮ ሰለ ወረረሸኙ  በርካታ መረጃዎች በመስራጨት ላይ ይገኛሉ። ያም ሆኖ አንዳንዶቹ መረጃዎቸ ሳይንሳዊ መሰረት የሌላቸዉና የተሳሳቱ ሆነዉ የሚገኙበት ሁኔታም አለ። ይህንን ብዠታ ለማስወገድ መዓዛ በምልክት ቋንቋ የምታደርሰዉን መረጃ  የታወቁና ታማኝ የመረጃ ምንጮችን አንደምትጠቀም ትገልጻለች። 
ምንም አንኳ የኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጰያ ከተከሰተ ወዲሀ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎቸ በጣት የሚቆጠሩ ቢሆኑም ቀደም ሲል ወረረሸኙ ከተከሰተባቸዉ ሀገሮቸ ልምድ አንደታየዉ ተገቢዉ ጥንቃቄ ካልተደረገ ቫይረሱ የሚዛመትበት ፍጥነት ከፍተኛ ነዉ። በመሆኑም መስማት የተሳናቸዉን ጨምሮ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በኮቪዲ -19 ኮሮና ቫይረስ ላይ ግንዛቤ አንዲኖረዉ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ ማድረስ የመከላከሉ ስራ አንዱና ዋነኛዉ አካል ነዉ። በዚሀ ረገድ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነዉ። 
ዓለምአቀፍ ስጋት የሆነውን ኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ስብሰባዎች፣ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና ስፖርታዊ ክንውኖች  ለሁለት ሳምንታት እንዳይካሄዱ ተድርጓል።
የቫይረሱ ስርጭትን ለመከላከል አለመጨባበጥ፣ የበሽታው ምልክት ከሚያስነጥሱና ካለባቸው ሰዎች መራቅ፣ እጅ ሳይታጠብ ዓይን፣ አፍና አፍንጫ አለመንካት፣እጅን በሳሙና አዘዉትሮ መታጠብ፣ ሰዎች ወደሚበዙበት ቦታዎች በተለይ የሕመም ስሜት ካለ አለመሄድ፣ በየተኛዉም ቦታ መስኮቶችን መክፈት ጠቃሚ ነዉ። በቫየረሱ መጠቃቱየታወቀ ሰዉ ደገሞ የህክምና አርዳታ አስኪገኝ ድረስ ራስን ከሌሎች ሰዎቸ መለየት በሚያሰነጠስበት ጊዜ አፍንጫን በመሃረብ ወይም በሶፍት መሸፈን አልያም በክንድ ላይ ማስነጠስ ቫየረሱ ወደ ሌሎች ሰዎቸ አንዳይዛመት ያደርጋል የባለሙያዎቹ ምክር ነዉ። 

ፀሐይ ጫኔ 

እሸቴ በቀለ
 

Audios and videos on the topic