በማድመጥ መማር ከራድዮ ወደ መድረክ | አፍሪቃ | DW | 12.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

በማድመጥ መማር ከራድዮ ወደ መድረክ

6 ወራት ጉልበታቸው ሲበዘበዝ ከርሞ ወደ መንደራቸው የተመለሱትን ህፃናት እህት ና ወንድም ማሊክና ፔምባን እንኳን ደህና መጣችሁ ይሏቸዋል ። ሎሚ ቶጎ ውስጥ ለመድረክ የበቃው ይህ የበማድመጥ መማር የራድዮ ድራማ ትኩረት በተለይ በምዕራብ አፍሪቃ የእለት ተዕለት ፈተና በሆነው የህፃናት የጉልበት ብዝበዛና ና የህፃናት ንግድ ላያ ነው ።

በተለያዩ የአፍሪቃ አገራት የሚሰራጨው የዶቼቬለው የበማድመጥ መማር የራድዮ ድራማ  ምዕራብ አፍሪቃ በምትገኘው በቶጎ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመድረክ በቅቷል ።  ቲያትሩን በመድረክ ያቀረቡት በዶቼቬለ የበማድመጥ መማር ፕሮጀክት የተዘጋጀውን ውድድር ያሸነፉ ቶጎ ዋና ከተማ ሎሜ ውስጥ የሚገኝ የወጣቶች ክበብ አባላት ናቸው ። የዶቼቬለው ፍሪድሪከ ሙለር በስፍራው ተገኝቶ ነበር ። ያዘጋጀውን ዘገባ ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።

የመንደሩ ነዋሪዎች ተጠሪያቸውን ያስተዋውቃሉ ። ተጠሪው በዘበኞች ታጅቦ ግርማ ሞገስ ባለ ሁኔታ ወደ መድረኩ ብቅ በማለት በባዕድ አገር 6 ወራት ጉልበታቸው ሲበዘበዝ ከርሞ ወደ መንደራቸው የተመለሱትን ህፃናት እህት ና ወንድም ማሊክና ፔምባን እንኳን ደህና መጣችሁ ይሏቸዋል ። ሎሚ ቶጎ ውስጥ ለመድረክ የበቃው ይህ የበማድመጥ መማር የራድዮ ድራማ ትኩረት በተለይ በምዕራብ አፍሪቃ የእለት ተዕለት ፈተና በሆነው የህፃናት የጉልበት ብዝበዛና ና የህፃናት ንግድ ላያ ነው ።

የገፀ ባህርያቱ የማሊክና የፔምባ አክስት ሁለቱን ልጆች ለመንከባከብና ለማስተማር ቃል ገብተው ነበር ከወላጆቻቸው ነጥለው የወሰዱዋቸው ። ሆኖም ማሊክና ፔምባ በሄዱበት ትምህርት ቤት አልተላኩም ፤ ከዚያ ይልቅ ለአንድ የናጠጠ የመሬት ከበርቴ ሌት ተቀን ጉልበታቸውን ሲገብሩ ነበር የከረሙት ።

ወደ መድረክ ቲያትር ተቀይሮ በቀረበው የበማድመጥ የራድዮ ድራማ ትወና 35 ተዋንያን ተካፍለዋል ። ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ሲተውኑ የመጀመሪያቸው ነው ። ከነዚህም አንዷ ሜሻንክ ግናሮ ናት 11 አመቷ ነው ።

« በተለይ ከማሊክ ጋራ በመተወኔ አዝናንቶኛል ፤ አበረታቶኛል ፣ አንዳንድ ምክሮችም ለግሶኛል ። ብዙ ተመልካች እንደሚኖር ሳስብ መጀመሪያ ላይ ፈርቼ ነበር ።  ሰዎቹን ሳያቸው ግን ፍርሃቴ ጠፍቶ በሥራ መርካት ጀመርኩ ። »

ሜሻንክና ሌሎቹ ተዋናዮች ቲያትሩ ለዝብ ከመቅረቡ በፊት ለአንድ ሳምንት ያህል በሎሜው የጎይቴ የባህል ቷቋም ሲለማመዱ ቆይተዋል ። በቲያትር ዓውደ ጥናት የተካተተው ይህ ልምምድ ለክበቡ የተበረከተው ሽልማት አካል ነው ። በነ ፔምባ ታሪክ ላይ ያተኮረው የበማድጥ መማር የራድዮ ድራማ በተለያዩ የአፍሪቃ አገራት በበጋው ወራት ተላልፏል ።

« ምድራችን የኛ ናት» በተባለው መንግሥታዊ ባልሆነ ድርጅት ውስጥ የሚሰራው የቲያትሩ ሃሳብ አፍላቂ ቡሎፌይ ቤዌዚማም የመጀመሪያው ደረጃ ሽልማት ካገኙት አንዱ ነው ። የቲያትር መመህር ሉክ አላንዳ ኩቢዲና ሎሜ ውስጥ በቀረበው በዚህ ቲያትር ልምምድ ላይ እገዛ አድርገል ። ኩቢዲና እንደሚሉት ለቲያትሩ ስኬት የተዋናዮቹ ሚና የጎላ ድርሻ ነበረው ።

« ቲያትሩ ስኬታማ እንዲሆን ታሪኩን እንደራሳቸው ታሪክ አድርገው መውሰድ ይኖርባቸዋል ። የተውኔቱ አብዛኛው ክፍል ባህልና ልምዳችንን መልሰን እንድናጤን እድሉን ፈጥሮልናል ። ለህፃናትና ወጣት ተዋንያኑ ራሳቸውን ከታሪኩ ጋር ማዋሃዱ በጣም ቀላል ነበር ። ለቲያትሩ ስኬት ተውኔቱ በፈረንሳይኛ ብቻ ሳይሆን በተዋናዮቹ የአፍ መፍጫ ቋንቋም ጭምር መተወኑ  ተጨማሪ አስተዋፅኦ አድርጓል ። ኢማኩሌ ኒዮን ሁ ጉልበታቸው ሲበዘበዝ ከርሞ የተመለሱት የማሊክና የፔምባን እናት ገፀባህርይ ተልባሳ ተውናለች ።

«ቲያትሩ ለኔ እጹብ ድንቅ ነው ።  ታሪኩ በተለይ በህፃናት ጉልበት ብዝበዛና ሽያጭ ላያ ያተኮረ በመሆኑ ወድጄዋለሁ ። ይህ በአሁኑ ጊዜ በሃገራችን ትልቅ ጉዳይ ነው ። በቲያትሩ አማካይነት ህዝቡ ስለ ህፃናት መበት ግንዛቤው እንዲዳብር ማድረግ ይቻላል ብዮ አስባለሁ »

። ህፃናትን ከአቅማቸው በላይ ማሰራትና የመሳሰሉት ለተዋናዮቹ አዲስ አይደለም ። አኑ ላ ፕላኔት « ምድራችን የኛ ናት» በተሰኘው ድርጅት ሥር እንደመታቀፋቸው በየጊዜው በጉዳዩ ላይ ይነጋገራሉ ። ድርጅቱ ከአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ጎን ለጎን በህፃናት በተለይም በልጃገረዶች መብት ላይ ይሰራል ። የገፀባህርያቱ የማሊክና የፔምባ ታሪክ ፍፃሜ አስደሳች ነው ። ወደ መንደራቸው ተመልሰዋል ። ምን ያህሉ የቶጎ ህፃናት ይህ አይነቱ እድል ሊገጥማቸው እንደሚችል ማወቁ ግን አስቸጋሪ ነው ።

ፍሪድሪከ ሙለር

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic