በማዕከላዊ ጎንደር፦ 55 ሺህ ተማሪዎች ትምህርት አልጀመሩም  | ኢትዮጵያ | DW | 24.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በማዕከላዊ ጎንደር፦ 55 ሺህ ተማሪዎች ትምህርት አልጀመሩም 

ከመስከረም ወር መጀመሪያ አንስቶ በምእራብ እና ማእከላዊ ጎንደር በተከሰቱ ግጭቶች የተነሳ በርካታ ሺህ ተማሪዎች ትምህርት አለመጀመራቸው ተገለጠ። በርካቶችን ለሞት፣ ለአካል ጉዳትና ለመፈናቀል  በዳረገው ግጭት የተነሳ፦ ከተማሪዎቹ የትምህርት መስተጓጎል በተጨማሪ አንዳንድ ተቋማት ሥራ አለመጀመራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገራሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:44

በርካታ ሺህ ተማሪዎች ትምህርት አልጀመሩም

ከመስከረም ወር መጀመሪያ አንስቶ በምእራብ እና ማእከላዊ ጎንደር በተከሰቱ ግጭቶች የተነሳ በርካታ ሺህ ተማሪዎች ትምህርት አለመጀመራቸው ተገለጠ። በርካቶችን ለሞት፣ ለአካል ጉዳትና ለመፈናቀል  በዳረገው ግጭት የተነሳ፦ ከተማሪዎቹ የትምህርት መስተጓጎል በተጨማሪ አንዳንድ ተቋማት ሥራ አለመጀመራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገራሉ። 2011 ዓም ከጠባ ወዲህ በ80 ትምህርት ቤቶች የሚማሩ 55 ሺህ ግድም ተማሪዎች በወቅቱ በተፈጠረው ግጭት የተነሳ አሁንም ድረስ ትምህርት አለመጀመራቸውን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ዞን ዐስታውቋል። ዓለምነው መኮንን ከባሕር ዳር ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል። 

በዓመቱ መጀመሪ በማዕከላዊ ጎንደር አካባቢ በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት በ80 ትምህርት ቤቶች የሚማሩ 55 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ትምህርት አልጀመሩም ሲል የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ዐስታወቀ። በተገኘው አንፃራዊ ሰላም የትራንስፖርትና የጤና አገልግሎት የተሻሻለ ቢሆንም ሥራ ያልጀመሩ ተቋማት እንዳሉ ደግሞ የአካባቢው ነዋሪዎች ናገራሉ። 

ከዓመቱ መጀመሪያ ጀምሮ በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በተከሰተው ግጭት በርካቶች ለሞት፣ ለአካል ጉዳትና ለመፈናቀል መዳረጋቸው ይታወሳል፡፡ ችግሩ እየከፋ በመሄዱም የክልሉ መንግስት የፀጥታ ኃይል ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት በአካባቢው አንፃራዊ ሰላም ማምጣት ችሏል፣ ሆኖም አንዳንድ የመንግስት ተቋማት ሥራ መጀመር እንዳልቻሉ ሰላሙም አንፃራዊ እንደሆነ የአይከል ከተማ ነዋሪ ለዶይቸ ቬለ DW በስልክ ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ በትራንስፖርትና በጤና ተቋማት አገልግሎት በኩል የጎላ ችግር እንደሌለ የተናገሩት እኝህ ግለሰብ ከጭልጋ የሚነሱ የህዝብ ትራንስፖረት ተሸከርካሪዎች መቃን አያልፉም ብለዋል፡፡ 

Fasil Schloss Gonder Äthiopien

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ርካብ በጭልጋ ቁጥር ሁለት፣ በምዕራብና ምስራቅ ደንቢያና በአርማጭሆ 14 ትምህርት ቤቶች ሥራ የጀመሩ ቢሆንም ከ55 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ማስተናገድ የሚሉ በጭልጋ ቁጥር ሁለት የሚገኙ 80 ትምህርት ቤቶች ሥራ አልጀመሩም ነው ያሉት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ መምህራንም ያለስራ መቀመጣቸውን አብራርተዋል፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ጉዳዩን አስመልክተው እንዳብራሩት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች የማካካሻ ታምህርት ይሰጣቸዋል። የወረዳው፣ የዞኑና የክልል የትምህርት አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ትምህርት ቤቶቹ እንዲከፈቱ ከፍተኛ ጥረት እደረጉ መሆናቸውንም ዶ/ር ይልቃል ተናግረዋል፡፡ ከክልሉ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ማስተባበሪ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚመለክተው በተከሰተው ግጭት ከምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን
ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

Audios and videos on the topic