በማሊ እና በናይጀርያ የሚታየው ውዝግብ | አፍሪቃ | DW | 07.05.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

በማሊ እና በናይጀርያ የሚታየው ውዝግብ

ምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሀገር ማሊ ውስጥ እአአ ባለፈው መጋቢት 2012 ዓም መጨረሻ መፈንቅለ መንግሥት ባካሄዱት የጦር ኃይል አባላት እና ከሥልጣን ባስወገዱዋቸው የቀድሞው ፕሬዚደንት አማዱ ቱማኒ ቱሬ ደጋፊ ወታደሮች መካከል ሰሞኑን ብርቱ ግጭት ተፈጥሮአል።

ምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሀገር ማሊ ውስጥ እአአ ባለፈው መጋቢት 2012 ዓም መጨረሻ መፈንቅለ መንግሥት ባካሄዱት የጦር ኃይል አባላት እና ከሥልጣን ባስወገዱዋቸው የቀድሞው ፕሬዚደንት አማዱ ቱማኒ ቱሬ ደጋፊ ወታደሮች መካከል ሰሞኑን ብርቱ ግጭት ተፈጥሮአል።

ከዚህ በተጨማሪ ሀገሪቱ በሰሜናዊ ከፊልዋየሚንቀሳቀሱ የቱዋሬግ ዓማፅያን መፈንቅለ መንግሥቱን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም አዛዋድ የተባለ ፡ ግን እስካዛሬ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላገኘ ነፃ መንግሥት ባቋቋሙት ድርጊት የመከፋፈል ሥጋት ተደቅኖባታል። ይህ ርምጃቸውም ኒዠርን ወደመሳሰሉ ወደሌሎች ጎረቤት የሳህል ሀገሮች እንዳይስፋፋ አሥግቶዋል።

በሌላ ሂደት ደግሞ በሰሜናዊ ናይጀርያ የሚንቀሳቀሰው አክራሪው የሙሥሊሞች ቡድን ቦኮ ሀራም ካለፉት ጥቂት ጊዚያት ወዲህ ጥቃቱን እያጠናከረ እና እያስፋፋ የተገኘበት ድርጊት ናይጀርያን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፉን ማህበረሰብም እያሳሰበ መጥቶዋል። ትኩረት በአፍሪቃ በነዚህ ሁለት ጉዳዮች ላይ የተጠናቀረ ዘገባ አለው።

አርያም ተክሌ
መሥፍን መኮንን

Audios and videos on the topic

 • ቀን 07.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14qbf
 • ቀን 07.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14qbf