በሙስና የተጠረጠሩ ሰዎችን ማሰር መቀጠሉ | ኢትዮጵያ | DW | 23.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በሙስና የተጠረጠሩ ሰዎችን ማሰር መቀጠሉ

የፌደራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የስነምግባር ትምሕርትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አሰፋ እንደተናገሩት እስካሁን በአጠቃላይ 51 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ለዶቼቬለ ተናግረዋል

Anti-Korruption Kommission - Sprecher, Mr. Berhanu Assefa. Yohannes Gegziabher(DW Amh. Korri in Addis Abeba) 13.05.2013

አቶ ብርሃኑ


የኢትዮጵያ መንግሥት በሙስና የተጠረጠሩ ተጨማሪ ሰዎችን በቄጥጥር ሥር መዋሉን ፣ በተያዙትና ጥቆማ በተደረገባቸው ሰዎች ላይም ምርመራው መቀጠሉን አስታወቀ ። የፌደራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የስነምግባር ትምሕርትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አሰፋ እስካሁን በአጠቃላይ 51 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። በሙስና ተጠርጥረው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ወደፊት እንደሚጨምርም አስታውቀዋል ። መንግሥት ከጥቂት ሳምንታት በፊት ስለ ጀመረው ስለዚሁ የማሰር ዘመቻ አቶ ብርሃኑ አሰፋን በስልክ አነጋግረናል ።
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic