በመጪው ዓመት ምርጫ ማካሄድ ይቻል ይሆን? | ኢትዮጵያ | DW | 02.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በመጪው ዓመት ምርጫ ማካሄድ ይቻል ይሆን?

ኢትዮጵያ በሕገመንግሥቱ መሠረት በመጪው ዓመት ግንቦት ወር ምርጫ ታካሂዳለች ተብሎ ይጠበቃል። የቦርድ አባላቱን ለማሟላት ገና በሂደት ላይ የሚገኘው ብሔራዊ የምርጫ ለምርጫ ሥራ ማስኬጂያ ከ3,5 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ በጀት ጠይቋል። መንግሥት እና አንዳንድ ፓርቲዎች ምርጫው በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት መካሄድ ይኖርበታል ባይ ናቸው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 30:04

«ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመጨረሻው መገለጫ ነው»

በሌላ ወገን ደግሞ ምርጫ ለማካሄድ አስቀድሞ መሟላት የሚገባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች መኖራቸውን በመዘርዘር ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ ተፈላጊውን ማከናወን ይቀድማል የሚሉ ወገኖች አሉ። የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ፣ የምርጫ አስፈጻሚ መዋቅሮች ዝግጅት፣ በየክልሉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያልተገደበ እንቅስቃሴ ማድረግ ፤ የሕግ እና የፍትህ ተቋማት ገለልተኛነት፣ በሀገሪቱ የሚታየው ያልሰከነ የመፈናቀል እና የፀጥታ ጉዳይን  ቅድሚያ ሰጥቶ ደርዝ ማስያዝያ እንደሚገባ በማሳሰብም ፤ በዚህ ይዞታ ምርጫ አሁን ዋነኛው አሳሳቢ ጉዳይ እንዳልሆነም ያስረዳሉ። ከ100 የሚበልጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባሉባት ሀገር በቦርዱ በኩል እስካሁን አስፈላጊውን አሟልተው የተመዘገቡት 68 ፓርቲዎች መሆናቸውን ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ዶይቼ ቬለ ለዚህ ሳምንት ኢትዮጵያ በመጪው ዓመት ምርጫ ማካሄድ አለባትን? ሲል ውይይት አካሂዷል።  ሙሉውን ውይይት ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች