በመንግሥት ግልበጣ ተጠርጥረው የታሰሩት የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች | ኢትዮጵያ | DW | 05.04.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በመንግሥት ግልበጣ ተጠርጥረው የታሰሩት የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች

ባለፈው ዓርብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት 8 የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሠራተኞችን ጨምሮ ዛሬ በከተማዋ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተሰየመው ችሎት የቀረቡት 10 ተጠርጣሪዎች ናቸው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:19

«ባለፈው ዓርብ ነው የታሠሩት»

ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ 10 የጂማ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ሕዝብን ለሁከት በማነሳሳት፣«ኦነግ ሸኔ» የተባለን ሸማቂ ቡድን በገንዘብና በሃሳብ በመደገፍ መንግሥትን ለመገልበጥ አሲረዋል በሚል መጠርጠራቸውን የአንዱ ቤተሰብ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። ባለፈው ዓርብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት 8 የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሠራተኞችን ጨምሮ ዛሬ በከተማዋ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተሰየመው ችሎት የቀረቡት 10 ተጠርጣሪዎች ላይ የተመሰረተው ክስ ፖሊስ መረጃውን ለማጠናቀር ከጠየቀው 14 ቀናት 10ሩ ተፈቅዶ ለሚያዚያ 07 ቀን 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ነው የተገለጸው። ከተጠርጣሪዎቹ የዩንቨርሲቲው የቀድሞ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ልማት ኃላፊ ይገኙበታል። በሌላ በኩል የጂማ ዩኒቨርሲቲ ከወራት በፊት የ2012 ዓ.ም. ተመራቂ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ወደ መድረክ ወጥቶ እነ አቶ ጃዋር መሃመድ እና ሌሎች ይፈቱ ሲል የተናገረውና በሌሎች ወንጀሎች መጠርጠሩ ተገልፆ የነበረው መሃመድ ዴክሲሶ አሁን ላይ የት እንዳለ እንደማያውቁ ወንድሙ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡

ስዩም ጌቱ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች