በመቅዲሾ-የታጣቂዎች ጥቃት | የሶማልያ ውዝግብ | DW | 11.12.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የሶማልያ ውዝግብ

በመቅዲሾ-የታጣቂዎች ጥቃት

በሶማልያ መዲና መቅድሾ ሽምቅ ተዋጊዎች የሚያደርሱት ጥቃት እያየለ መምጣቱ ተነገረ። ትናንት በመቅዲሾ ታላቅ ገበያ በባካራ ሽምቅ ተዋጊዎች ከመንግስት ወታደር ጋር ባስነሱት ተኩስ ሁለት ግለሰቦች እና አምስት ያህል ነዋሪዎች መቁሰላቸዉ ተገልጾአል። በሌላ በኩል በሰሜናዊ መቅዲሾ በቡሌ ቡርቴ መንደርን ሽምቅ ተዋጊዎች በኢትዮጽያ የሚታገዘዉን የሶማልያ ሽግግር መንግስት ለጥቂት ግዜያት አስለቅቀዉ እንደነበር እና የሶማልያ የጎሳ መሪዎች የመንግስት ወታደሮች

default

��ንዲመለሱ መጠየቃቸዉ የሮይተርስ የዜና ወኪል ባወጣዉ ዘገባ ጠቅሶአል

በመቅድሾ ዛሪ ሰላም የሰፈነ ይመስላል፣ ያለን በመቅድሾ የሚገኘዉ የሻቤለ ጋዜጠኛ ራሽድ ሞሃመድ፣ እንደገለጸዉ በሳምንቱ መጨረሻ ከሰሜናዊ መቅድሾ 220 ኬሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዋ በቡሌ ቡርቴ መንደር ሽምቅ ተዋጊዎች በኢትዮጽያ በሚታገዘዉን የሶማልያ የሽግግግር መንግስት ወታደሮች የጦር ሰፈር አስለቅቀዉ ነበር። ሽምቅ ተዋጊዎቹ መንደሩን ያስለቀቁት በጥቂት ሰአታት ዉግያ ነበር። በአካባቢዉ የሚገኙ ጎሳዎች ስምቅ ተዋጊዎቹ መንደሩን ከያዙ በኳላ ጥያቅያቸዉ የቀረጥ ጥያቄ በመሆኑ ነበር የመንግስት ወታደሮች መልሰዉ እንዲሰፍሩ የጠየቁት። እንደ ጋዜጠኛ ራሽድ አገላለጽ፣ ስፍራዉ በተለይ የኢትዮጽያ ጦር ሰራዊት ጦር መንደር ነዉ። ስፍራዉንም በቁጥጥራቸዉ አድርገዉት ነበር። በአሁኑ ወቅት ግን ሰራዊቱ መልሶ ሰፍሮ ይገኛል፣ መቅድሾም ሰላማዊ ትመስላለች ሲል ገልጾአል። በተለይ ፋርጋህ እና መሃመዳን የተሰኘዉ የመቆጣጠርያ ኬላ ላይ የኢትዮጽያ ወታደሮች በመቆጣጠር ላይ ናቸዉ አክሎአል። ባለለፈዉ እሁድ በመቅዲሾ ባካራ ተብሎ በሚጠራዉ ትልቅ የገበያ ስፍራ የሽግግር መንግስቱ ወታደሮች ሸማቂዎች ላይ ባስነሱት ተኩስ አንድ ሲቢል መገደሉልና በርካታ ነዋሪዎች መቁሰላቸዉንም ገልጾአል። እንደ ጋዜጠና ራሽድ በመቅዲሾ በየግዜዉ በሚከሰተዉ ጥቃት ሲቢል ነዋሪዎች እየተጎዱ ናቸዉ። መቅዲሾ በድንገት አንድ ትልቅ ብጥብጥ እና ጦርነት የሚያገረሽበት ስፍራ በመሆኑም ነዋሪዎችዋ በፍርሃት እና በጭንቀት ላይ ናቸዉ። በተለይ ሽምቅ ተዋጊዎቹ በመንግስት የጸጥታ አስከባሪዎች እና በኢትዮጽያ ጦር ሰራዊት ላይ የጥቃት ሙከራ በተደጋጋሚ ያነሳሉ ሲል ገልጾአል።
እንደ ተባበሩት መንግስታት መግለጫ በመቅድሾ እና አካባቢዋ ከአንድ አመት ግድም ጀምሮ በተነሳዉ ከባድ ሁከት ከስድስት መቶ ሺህ ህዝብ በላይ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሎአል።