1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በመራዊው ግጭት ከ80 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ፤ ኢሰመጉ

ሐሙስ፣ ጥር 30 2016

ሰሞኑን በአማራ ክልል ከባሕር ዳር 35 ኪሎ ሜትር በምትርቀው የመረዓዊ ከተማ በመከላከያና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በነበረ ግጭት ከ80 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ አስታውቋል። አንድ የመረዓዊ ከተማ ነዋሪ በወቅቱ በነበረው ውጊያ የተገደሉ የ83 ሰዎችን ቀብር ማየታቸውንና ቁሳዊ ንብረት መውደሙንም ገልጠዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4cBL2
Logo des Ethiopian Human Rights Council
ሰሞኑን በአማራ ክልል ከባሕር ዳር 35 ኪሎ ሜትር በምትርቀው የመረዓዊ ከተማ በመከላከያና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በነበረ ግጭት ከ80 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ አስታውቋል።ምስል Ethiopian Human Rights Council

በአማራ ክልል መራዌ ከተማ በነበረው ውጊያ 83 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

ሰሞኑን በአማራ ክልል ከባሕር ዳር 35 ኪሎ ሜትር በምትርቀው የመረዓዊ ከተማ በመከላከያና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በነበረ ግጭት ከ80 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ አስታውቋል። አንድ የመረዓዊ ከተማ ነዋሪ በወቅቱ በነበረው ውጊያ የተገደሉ የ83 ሰዎችን ቀብር ማየታቸውንና ቁሳዊ ንብረት መውደሙንም ገልጠዋል፡፡

በክልሉ ያለው የሰላም ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መምጣቱን የጠቀሰው ኢሰመጉ ችግሩ እልባት ባለማግኘቱ አሁንም የሰብአዊ ጥሰቶች በአማራ ክልል መቀጠላቸውን ገልጧል፡፡

ኢሰመጉ ጥር 28/2016 ዓ ም ባወጣው መግለጫ፣ “በመረዓዊ ከተማ ጥር 20/2016 ዓ ም በመንግስት የፀጥታ ኃይሎችና በታጣቂ ቡድኖች መካከል በነበረ ግጭት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈፀማቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች ደርሰውኛል፡፡” ብሏል፡፡

መደራደር ለሚፈልጉ የታጠቁ ኃይሎች በሩ ክፍት ነው ፤ የአማራ ክልል መስተዳድር

ኢሰመጉ በመግለጫው ግጭቱን ተከትሎ በወቅቱ  የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በከተማዋ መቋረጡን አስታውሷል፤ በነበረው ግጭት ተሳትፎ በሌላቸው ሰዎች ላይም ግድያ፣ የአካል ጉዳት፣ ድብደባ፣ ማስፈራሪያና ሌሎችም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈፀማቸውን ማረጋገጥ መቻሉን  አመልክቷል፡፡

በግጭቱ ሁለት ሴቶችንና አንድ የ17 ዓመት ታዳጊን ጨምሮ ከ80 በላይ  ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመጉ በመግለጫው አሳውቋል፡፡ ለግድያውም ምከንያት የነበረው በከተማዋ የነበረው ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ነበር ሲል ኢሰመጉ አክሏል፡፡ የሟቾች አስከሬን በከተማው በሚገኘው ማሪም ቤተክርስቲያን ከጥር 21/2016 ዓም ጀምሮ እንደተፈፀመም ከነዋሪዎች አገኘሁ ያለውን መረጃ ጠቅሶ ኢሰመጉ ገልጧል፡፡

ከፍተኛ የመብት ጥሰት በከተማዋ በመድረሱ የአካባቢው ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቅቀው መውጣታቸውንም መግለጫው ጠቁሟል፡፡ኢሰመጉ የአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ ሲሻሻል ተጨማሪ የምርመራ ስራ በማከናወን ዝርዝር መግለጫ ወደፊት እንደሚሰጥም አመልክቷል፡፡

Äthiopien | Kämpfer der Fano-Miliz in Lalibela in der nördlichen Amhara-Region
ምስል Solan Kolli/AFP/Getty Images

በወቅቱ በከተማዋ የነበረውን ጦርነት የተመለከቱ ስማቸው እንዳይጠቀስና ድምፃቸው እንዲቀየር የፈለጉ አንድ  የመረዓዊ ከተማ ነዋሪ በእለቱ ከፍተኛ ተኩስ ነበር፣ በየቦታው ሰዎች ተገድለው በቀጣዩ ቀን ( ከጥር 21/2016 ዓ ም ጀምሮ በነበሩ ተከታታይ ቀናት) የ83 ሰዎች አስከሬን በማሪያም ቤተክርስቲያን ሲቀበር ማየታቸውን፣ ከ18 በላይ ባለ ሶስት እግር (ባጃጆች) መቃጠላቸውን ማየታቸውንና እረሳቸውም ከሞት በተዓምር ማምለጣቸውን ነግረውናል፡፡በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ የከፋዉ ግጭት

የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ በመራይ ስለነበረው ጦርነት ተጠይቀው የሚከተለውን ምለሽ ሰጥተው ነበር፡፡

“መረዓዊም ሆነ ሞጣ ሌሎችም በክልሉ ውስጥ ባሉ አካባቢዎችም ከቀን ቀን ተመርጦ የፀጥታ መዋቅሩ እንቅስቃሴና ሁኔታ ክፍተት አለው ተብሎ በታሰበበት ሁኔታና ሰዓት ሁሉ ሙከራ ይደረጋል፣ ግን ሙከራው አይሳካም፣ ህይወት በዚያም በዚህም ያስከፍላል ሰላምና ደህንነት የሚያስከብር አካል ይህንን ኃላፊነት ወስዶ ማስተካከልና ማረም ለህዘብና ለማህበራዊ እንቅስቃሴ ተግዳሮት እንዳይሆን ማድረግ ነው ዋናው፡፡”

በክልሉ የታወጀው የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ አስፈፃሚው አካል የተሰጠውን ከፍተኛ ስልጣን አስፋፍቶ በመጠቀሙ በርካታ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በዋናነትም እስራት በብዙ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በአዲስ አበባና በአማራ ክልል መፈፀሙን መረዳቱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ አስታውቋል፡፡በአማራ ክልል የኢንተርኔት መቋረጥ በባንክ አገልግሎት፣ በግብረ ሰናይ እና የምርምር ሥራዎች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ

በአዋጁ የተቋቋመው የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ መምሪያ እዝ መረጃዎችን በተገቢው ሁኔታ አያጋራም፣ የአስቸኳ ጊዜ አዋጁ የተፈፃሚነት ወሰን አለማስቀም ይህም መብቶችን ይገድባል ሲል ኢሰመጉ ተችቷል፡፡

በአማራ ክልል በተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ምክንያት ለሐምሌ 28 2015 ዓ ም ጀምሮ ለ6 ወራት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የቆየ ሲሆን የአዋጁ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ እንደገና ለ4 ወራት መራዘሙ ይታወሳል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ

ሸዋዬ ለገሰ