በሐረሪ ክልል ከሶስት መቶ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋል | ኢትዮጵያ | DW | 12.11.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በሐረሪ ክልል ከሶስት መቶ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋል

በሀረሪ ክልል በአሸባሪነት ከተፈረጁት የህወሀት እና ኦነግ ሸኔ ቡድኖች ጋር ግንኙነት አላቸው የክልሉን ፀጥታም በማደፍረስ ተጠርጥረዋል የተባሉ ከሶስት መቶ በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:50

የሐረሪ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት የድርሻችን እንወጣለን አሉ

በሀረሪ ክልል በአሸባሪነት ከተፈረጁት የህወሀት እና ኦነግ ሸኔ ቡድኖች ጋር ግንኙነት አላቸው የክልሉን ፀጥታም በማደፍረስ ተጠርጥረዋል የተባሉ ከሶስት መቶ በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ፡፡ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራምክር ቤት በበኩሉ በሀገሪቱ ላይ የተጋረጠውን የተቀናጀ አደጋ በመመከት ለድል እንበቃለን ብሏል፡፡

የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ አዩብ አህመድ ለዶይቼ ቬሌ በስልክ በሰጡት መረጃ እንዳስታወቁት በክልሉ በአሸባሪነት ከተፈረጁት የህወሀት እና ኦነግ ሸኔ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ያላቸው እና የክልሉን ፀጥታም በማደፍረስ የተጠረጠሩ ከሶስት መቶ በላይ ሰዎች እና የተለያዩ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

አቶ አዩብ በወንጀል ተጠጠርጥረው የተያዙ ሰዎችን ምርመራ የሚከታተል የምርመራ ቡድን መቋቋሙን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ድል ያለ መስዋዕትነት አይገኝም ያለው በክልሉ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያካተተው የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በበኩሉ በሀገሪቱ የተጋረጠውን ችግር በጋራ ለመፍታት ህብረተሰቡ የሚችለውን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል ፡፡

ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ሲያጋጥማት የነበሩ ችግሮችን ለመቀልበስ ልጆቿ ሲወጡ ሲወርዱ መኖራቸው ይታወቃል ያለውየጋራ ምክር ቤቱ በአሁን ሰዓት በሀገሪቱ ላይ የተጋረጠውን የተቀናጀ አደጋ በመመከት ለድል እንበቃለን ብሏል፡፡

በሀረሪ ክልል የፀጥታ ስጋትን ለመቅረፍ በሀገሪቱ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሰረት አድርጎ የሰዓት እላፊ እና ሌሎች እርምጃዎች በመወሰድ ላይ ናቸው፡፡

መሳይ ተክሉ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic