በልማት ስም የተፈናቀሉ አርሶአደሮች | ኢትዮጵያ | DW | 22.12.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በልማት ስም የተፈናቀሉ አርሶአደሮች

አርሶ አደሮቹ ከመሬታቸዉ ሲነሱ የካሳ ክፍያ ገንዘብ ብቻ ተሰጥተዉ ቦታዉን እንዲለቁ ከማድረግ ዉጭ ምንም አይነት ድጋፍና ክትትል አይረግም ነበር ያሉት ሀላፊዉ፤የካሳ አሰጣጡም ቢሆን እጥረት የነበረበትና የአርሶ አደሮቹን ህይወት ለችግር የዳረገ እንደነበር ገልጸዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:44

የተፈናቀሉ አርሶአደሮች ጉዳይ

 
በልማት ስም በአዲስ አባባና አካባቢዋ የሚገኙ አርሶ አደሮች ያለበቂ ድጋፍና የካሳ ክፍያ  ከይዞታቸዉ ሲፈናቀሉ መቆየታቸዉን በጥናት ማረጋገጡን መንግስት ገለጸ።የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እንደሚለዉ የተከፈለዉ ካሳ በቂ አልነበረም።የአርሶ አደሮቹን ህይወት ለችግር የዳረገም ነበር። በመሆኑም
በተያዘዉ በጀት አመት 20 ሺህ አርሶ አደሮችን መልሶ ለማቋቋም መታቀዱን ቢሮዉ ገልጿል። አስተያየት ሰጭወች በበኩላዉ የዘገየ ምላሽ ነዉ ብለዉታል። 

በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚገኙ  የኦሮሚያ ልዩ ዞን አርሶ አደሮች መሬታቸዉ ለተለያዩ የግንባታና የልማት ስራወች ይፈለጋል በሚል ከኖሩበት ቀየ
ያለ በቂ ካሳና ዝግጅት ሲፈናቀሉ ቆይተዋል ተብሎ በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ትችትን በህዝቡ ዘንድ ደግሞ ተቃዉሞን ሲቀሰቅስ ቆይቷል።
ችግሩ አርሶ አደሮቹንና ቤተሰቦቻቸዉን ለከፋ  ቀዉስ ሲዳርግ መቆየቱን አንድ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ነዋሪ 
ይናገራሉ። በአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ታምሩ መክት እንደገለጹት በተነሺ አርሶ አደሮቹ የደረሰዉ ማህበራዊ ችግር
በጥናት በመረጋገጡ በተያዘዉ በጀት አመት 20 ሺህ አርሶ አደሮችን መልሶ ለማቋቋም መታቀዱን ገልጸዋል።ተጠሪነቱ ለአዲስ አበባ ለሰራተኛና ማህበራዊ ቢሮ የሆነ የልማት ተነሽ አርሶ

አደሮች ማቋቋሚያ  ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት መቋቋሙንም ኃላፊዉ ተናግረዋል።አርሶ አደሮቹ ከመሬታቸዉ ሲነሱ የካሳ ክፍያ ገንዘብ ብቻ ተሰጥተዉ ቦታዉን እንዲለቁ ከማድረግ ዉጭ ምንም አይነት ድጋፍና ክትትል አይረግም ነበር ያሉት  ሀላፊዉ፤የካሳ አሰጣጡም ቢሆን እጥረት  የነበረበትና የአርሶ አደሮቹን ህይወት ለችግር የዳረገ እንደነበር ገልጸዋል።እንደ አቶ ታምሩ ገለጻ በየ ክፍለከተሞቹ  አርሶ አደሮቹን የመለየትና መረጃ የመሰብሰብ ስራ ይሰራል።ህይወታቸዉን በዘላቂነት ለማቋቋምም ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉት አስተያየት ሰጭ ግን በዚህ አይስማሙም። ችግሩ ለአመታት የተጠራቀመና ሰሚ አጥቶ የቆየ በመሆኑ ለአፈታት ያስቸግራል ባይ ናቸዉ።አብዛኛዉ አርሶ አደር በተለያዩ ቦታወች ያለቋሚ አድራሻ በመኖሩም ለማሳባስብም አስቸጋሪ ነዉ ይላሉ።ከአዲስ አበባ ከተማ መስፋፋት ጋር ተያይዞ «አርሶ አደሮችን  ከቀያቸዉና ከመሬታቸዉ ማፈናቀል ይቁም» በሚል በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች
ከአመት በላይ የዘለቀ ተቃዉሞ ሲካሄድ መቆየቱ  ይታወሳል። 


ፀሐይ ጫኔ

ነጋሽ መሀመድ 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች