በላይቤሪያ በጉልበት ብዝበዛ የተከሰሰዉ ኩባንያ | የጋዜጦች አምድ | DW | 16.12.2005
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

በላይቤሪያ በጉልበት ብዝበዛ የተከሰሰዉ ኩባንያ

በልማትና እድገት ስም በየአዳጊ አገራቱ መዋዕለ ንዋይ ከሚያፈሱ ኩባንያዎች አብዛኛዉቹ የሰብዓዊም ሆነ የህፃናት መብቶችን የማያከብሩ በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል። ከእነዚህ መካከልም ለረዥም ጊዜ በጎማ ዛፍ ተከላና ምርት ተግባር ላይቤሪያ የገባ አንድ ኩባንያ የህፃናትን ጉልበት ያለ አግባብ

በመበዝበዝና ሰራተኞችን ከተገቢዉ ሰዓት በላይ በማሰራቱ መሆኑ ተነግራል። ምንም እንኳን ኩባንያዉ የልማት ተስፋ ሰጥቶ ከላይቤሪያ የተፈጥሮ ሃብት ሊቋደስ ቢገባም አደርጋለሁ ያለዉን የልማት እቅድ በተግባር ባለማድረጉ ወቀሳ ገጥሞታል።

በላይቤሪያ መዋዕለ ንዋይ ካፈሰሱት የዉጪ ኩባንያዎች መካከል ብሪጅስቶን ፋየርስቶን የተባለዉ ነዉ የህፃናትን ጉልበት በመበዝበዝ፤ መርዛማ የተባይ ማጥፊያና ማዳበሪያ በማምረት ክስ የተመሰረተበት።
ኩባንያዉ ራሱን ሲያቀርብ የጤናና የትምህርት እንዲሁም የስልጠና እድሎች ጨምሮ ተገቢ የስራ እድል እንደሚያመቻች ነበር ተስፋ በመስጠት አንገቱን ያስገባዉ ላይቤሪያ።
ሆኖም ባለፈዉ ወር የዩናይትድ ስቴትስ የካሊፎርኒያ ፌደራል ችሎት ክስ የመሰረተበት ህፃናትን ለጉልበት ብዝበዛ በመቅጠር የጎማ ዛፍ ተከላዉን እንደሚያከናዉን በመጥቀስ ነዉ።
ክሱን የመሰረተዉ መቀመጫዉን ዋሽንግተን ያደረገ ዓለም ዓቀፍ የሰራተኞች መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅት ነዉ በ12 አዋቂና በ23 ህፃናት ሰራተኞች ስም።
ዋና መስሪያ ቤቱ በሰሜን አሜሪካ የሚገኘዉ ንብረትነቱ የጃፓኖች የሆነዉ ይህ ኩባንያ ግን ክሱን አስተባብሏል።
የክሱ ዝርዝር እንደሚያሳየዉ እነዚህ ሰራተኞች ከንጋቱ 10:30 በስራ ቦታቸዉ መገኘት አለባቸዉ በዕለቱ የሚጠበቅባቸዉን 750 የጎማ ዛፍ የመትከል ኮታ ለመሙላት።
ይህንንም ለማድረግ የግድ ልጆች አባቶቻቸዉን ወይም ሚስቶች ባሎቻቸዉን ተከትለዉ በመምጣት ሳይነጋ ጀምረዉ እስከ ዉድቅት መስራት ይኖርባቸዋል።
ከሳሹ ቡድን የኩባንያዉ ዋና መስሪያ ቤት ስለህፃናቱ ጉልበት መበዝበዝ ማወቅ ብቻ ሳይሆን ሁኔታዉን እንደሚያበረታታም ጨምሮ አጋልጧል።
ፋየርስቶን ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብቶችን በመጣስ ከሚታወቁት የዩናይትድ ስቴትስ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ይሁን እንጂ ብቸኛዉ እንዳልሆነም ይኸዉ ቡድን ይጠቅሳል።
ተመሳሳይ ክስ ከመሰረተባቸዉ ታዋቂ ኩባንያዎች መካከል ኔስትል፤ አርከር ዳኒኤል ሚድላንድና ካርጊል በካካዎ ማምረት ተግባር የተሰማሩ ህፃናትን በማሰቃየትና በህገወጥ መንገድ በማጓጓዝ ተከሰዋል።
በተጨማሪም አንዖካል የተሰኘዉ የበርማ፤ የህንዱ ዶዉ ኬሚካልና የኮሎምቢያዉ ኮካኮላ በሰብዓዊ መብት አለማክበር በተመሳሳይ በድርጅቱ ክስ የተመሰረተባቸዉ ኩባንያዎች ናቸዉ።
ክሱን አስመልክቶ ከሲኤንኤን ለቀረበላቸዉ ጥያቄ ኩባንያቸዉ የህፃናትን ሁኔታ በተመለከተ ጥብቅ ፖሊሲ እንዳለዉ በመጥቀስ ከ18ዓመት በታች የሆኑትን አንቀጥርም ሲሉ የፋየርስቶን ፕሬዝደንት ዳን አዶሚቲስ ምላሽ ሰጥተዋል።
ጨምረዉም ሰራተኞቻቸዉ ስለመብታቸዉ ከኩባንያዉ ጋር የሚከራከርላቸዉ ማህበር እንደመሰረቱና መልካም የሚባል ግንኙነት እንዳቸዉ ለማስረዳት ሞረዋል።
የላይቤሪያ የፕሬዝደንታዊ ጉዳይ ሚኒስትር ጃክሰን ኢ ዶይ በበኩላቸዉ ፋየርስቶን የተባለዉ ኩባንያ መዋዕለ ንዋይ በአገራቸዉ ለማፍሰስ ሲዋዋል አደርገዋለሁ ያለዉን ሁሉ እንደጠበቅነዉ አላደረገም ይላሉ።
ኩባንያዉ በገነባዉ ህንፃ ዉስጥ ከሚኖሩት መካከል ተጠይቀዉ እንደገለፁት ህንፃዎቹ የዉሃ፤ የመፀዳጃም ሆነ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የላቸዉም።
ኩባንያዉ በበኩሉ የቀረበበትን ትችትና ቅሬታ በላይቤሪያ ለ14ዓመታት በዘለቀዉ የእርስ በርስ ግጭትና አሳቧል።
አማፅያኑ፤ መንግስትና የሲቪል ማህበራት የተዉጣጡበት የአገሪቱ ብሄራዊ የሽግግር መንግስት በቅርቡ በተካሄደዉ ምርጫ መሰረት ተለዉጦ አሁን ሁኔታዎች በላይቤሪያ ተቀይረዋል።
ኤለን ጆንሰን ሲርሊፍ በአፍሪካ የመጀመሪያ ሴት ፕሬዝደንት በመሆን በላይቤሪያ ሲመረጡ በአገሪቱ ሙስናን በመዋጋት የሥራ ዕድል በመፍጠር የዉሃና የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ለማስፋፋት ቃል ገብተዋል።
23ኛዋ የላይቤሪያ ፕሬዝደንት ሲርሊፍ ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግር እንደገለፁት አዲሱ የእሳቸዉ አስተዳደር በአገራቸዉ ባህልን፤ ፖለቲካንና የብሄረሰብ ስብጥርን እንዲሁም መብቶችን በተመለከተ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።