በላሊበላ ላይ የተደረገው ቅድመ ጥናት ተገመገመ | አውሮጳ እና ጀርመን | DW | 16.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ እና ጀርመን

በላሊበላ ላይ የተደረገው ቅድመ ጥናት ተገመገመ

የፈረንሳይ የቅርስ ጥናት ባለሙያዎች በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት ላይ ያደረጉትን የቅድመ ጥናት የገመገመ ውይይት በፓሪስ ተካሄደ። በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት የተካሄደው ውይይት በቅርሱ ላይ ያንዣባበውን አደጋ ለመከላከል የሚያስችል የወደፊት አቅጣጫዎች የተቀመጡበት ነው ተብሏል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:12

በላሊበላ ላይ የተደረገው ቅድመ ጥናት ተገመገመ

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም  ቅርስነት በተመዘገበው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት ቅርስ ላይ ያንዣባበውን የአደጋ ስጋት ለመከላከል እና ቅርሱንም ለመጠገን የፈረንሳይ የቅርስ ጥናት ባለሙያዎች ቅድመ ጥናት አካሂደዋል። በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ የዩኔስኮ ዋና መስሪያ ቤት ይህንኑ የምርመራ ውጤትን የገመገመ ውይይት ተደርጓል። ውይይቱ ለቀጣይ እርምጃዎችም አቅጣጫ ያስቀመጠ መሆኑ ተገልጿል።

የተለያዩ ባለሙያዎችን ከዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ቅርስ ጥናት ጥበቃ ማዕከል፣ መንግስታዊው ያልሆነው የሀውልቶች እና ታሪክ ቦታዎች ድርጅት እንደዚሁም የፈረንሳይ እና የኢትዮጵያ ተወካዮችም በጋራ መድረኩ ላይ ተካፋይ ሆነውበታል። በውይይቱም ጥናቱን መሰረት በማድረግ በቅርሱ ላይ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት የአካባቢውን ህብረተሰብ እና ቤተክርስቲያኒቱንም ባማከለ መልኩ ቅርሱን ለመታደግ የተግባር ስራ እንደሚደረግም ታውቋል። 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

ሃይማኖት ጥሩነህ

ተስፋለም ወልደየስ 

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic