በሊቢያ እና ስደተኞች ጉዳይ የመከረዉ የአዉሮጳ ኅብረት   | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 18.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

በሊቢያ እና ስደተኞች ጉዳይ የመከረዉ የአዉሮጳ ኅብረት  

የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትላንት በቤልጅየም ብራስልስ ስብሰባቸው በሊቢያ ፖለቲካ እና የስደተኞችን ጉዳይ ተወያይተው ውሳኔዎችን አሳልፈዋል። ሚኒስትሮቹ በሰ/ ኮሪያ ላይም ተወያይተው አካባቢውን ከኒዩክለር የጦር መሳሪያ ስጋት ለመታደግ ኅብረቱ ከዓ/አቀፉ ኅ/ሰብ ጋር በጋራ እንደሚሰራ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቀዋል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:55

የአውሮጳ ህብረት እና ስደተኞች

በተጨማሪም ሚኒስትሮቹ የዘንድሮው ዓመት ከፍተኛ የምግብ እጥረት እና የደህንነት ስጋቶች የተጋረጡበት ዓመት መሆኑን በመጥቀስ በተለይም በሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሰሜን ናይጄሪያ እና የመን ከፍተኛ የረሃብ አደጋ የተከሰተ መሆኑን አስገንዝበው በእነዚህ ሀገራት ሊደርስ የሚችለውን እልቂት ለማስቀረት ህብረቱ እና አባል መንግስታት የሚያደርጉትን ጥረት ሌሎች ለጋሽ ሀገሮችም እንዲያግዟቸው ጥሪ አቀርበዋል፡፡

ገበያው ንጉሴ 

ተስፋለም ወልደየስ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች