በለንደን በድርቅ ለተጎዱ የእርዳታ ስብስብ | ዓለም | DW | 28.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

በለንደን በድርቅ ለተጎዱ የእርዳታ ስብስብ

እንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የኪነጥበብ ባለሙያዎች ሀገር ዉስጥ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እርዳታ ማሰባሰቢያ የሚሆን ዝግጅት ታናንት አሰናድተዉ ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:03
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:03 ደቂቃ

በድርቅ ለተጎዱ እርዳታ

እኛዉ ለኛዉ በተሰኘዉ በዚህ ዝግጅትም እስከአምስት ሺህ የእንግሊዝ ፓዉንድ ሳይሰበሰብ እንዳልቀረ የዝግጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ፀሐፊ እና የገንዘብ ማሰባሰቢያዉን መድረክ የመሩት አቶ ወንድወሰን አበበ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። የኪነጥበብ ባለሙያዎቹ በድርቅ የተጎዱት ገበሬዎች የእርዳታ ስንዴ ከመጠበቅ ይልቅ ዉኃን አዉጥተዉ ለእርሻቸዉ የሚያዉሉበት መሣሪያ ወይም ቴክኒዎሎጂ እንደሚሹ በመረዳታቸዉም አቅማቸዉ በፈቀደ የዉኃ ማዉጫ ማሽን ገዝተዉ በድርቁ ክፉኛ ለተጎዱ አካባቢዎች እንኳ ለመስጠት ማሰባቸዉንም አስረድተዋል። የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ኮሚቴዉን ፀሐፊ ሸዋዬ ለገሠ በአጭሩ ስለዝግጅቱ ጠይቃቸዋለች።

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic