በህፃናት እና ወጣቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች | ባህል | DW | 08.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

በህፃናት እና ወጣቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች

አንድ ልጅ ወይንም አዳጊ ወጣት እየተደበደበ ተሰቃይቶ ሲያድግ በስነ ልቦናው ላይ መጥፎ ትውስታ ጥሎ እንደሚያልፍ ይታመናል። ተፅዕኖውም ለእድሜ ልክ አብሮ እንደሚቆይ ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

Symbolbild: Lehrer schlägt (misshandelt) ein Schüler in der Schule *** Quelle: Kudakyar Lizenz: Frei undatiert, eingestellt Juli 2011

በትምህርት ቤትም ልጆች ያለአግባብ ይቀጣሉ

አብዛኛውን ጊዜ በህፃናት ወይንም አዳጊ ወጣቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች በቤተሰብ ወይንም በቅርብ በሚያውቋቸው ሰዎች እንደሆኑ ይታሰባል። በርግጥ የጥቃቱ አይነት ይለያያል። አዘውትሮ መደብደብ፣ የወሲብ ጥቃትና የመሳሰሉት ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ስነ ልቦናን የሚጎዱ ጥቃቶች ናቸው። የዛሬው የወጣቶች አለም እንግዳችን የአካል ብቻ ሳይሆን የአዕምሮ ጠባሳዎች እንዳሉት ያጫውተናል። ለዛሬ ስሙን ዮናታን ብለንዋል። ዮናታን አባቱ ለስራ ወደ ኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር አካባቢ በሄዱበት ወቅት ተወለደ። አባቱ ስራቸውን እንደጨረሱም ዮናታንን ይዘው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ፤ ኋላም ከዮናታን እናት ጋ ሳይሆን ከሌላ ሴት ጋ ትዳር መሰረቱ ።

ይሁንና ዮናታን የአባቱ ትዳር መመስረት ለአዘውትሮ በአባት መደብደብ ብቸኛ ምክንያት እንደሆነ አያምንም። አባቱ በማንኛውም ሰዓት ሃይለኛ እንደነበሩ ነው ያጫወተን። ዮናታን የአባቱን ቤት ለቆ ወደ ጎዳና ሲወጣ «12 አመቴ እና የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ» ይላል። ወጣቱ ስለ በፊት ህይወቱ ማውራት አሁን ድረስ ይከብደዋል። ዮናታን ከቤት ወጥቶ ሲኖር አመታት ተቆጠሩ። ዛሬ የሚኖረው ኑሮ ይሻል ይሆን? መልስ ሰጥቶናል። ሙሉ ዝግጅቱን ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic