ቆይታ ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ ጋር | ባህል | DW | 06.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ቆይታ ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ ጋር

በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የዕፅዋትና የአካባቢ መስተጋብር ተመራማሪ ናቸዉ።የመጀመሪያ ዲግሪያቸዉን በሀሮማያ ዩንቨርሲቲ ፣ሁለተኛ ዲግሪያቸዉን በስዊድን ሀገር የዶክትሬት ዲግሪቸዉን በኔዘርላንድ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተከታትለዋል። በሙያቸዉ ሳይወሰኑ እመጓ፣ ዝጎራ፣ መርበብት በሚሉ ርዕሶች ታሪክን የሚያጣቅሱ መጽሐፎች አሳትመዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:57

ጽሑፎቻቸዉ ትዉልድን የሚገነቡ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል


በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የዕፅዋትና የአካባቢ መስተጋብር ተመራማሪ ናቸዉ።የመጀመሪያ ዲግሪያቸዉን በሀሮማያ ዩንቨርሲቲ ፣ሁለተኛ ዲግሪያቸዉን በስዊድን ሀገር የዶክትሬት ዲግሪቸዉን በኔዘርላንድ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተከታትለዋል።ያም ሆኖ ግን በሙያቸዉ ሳይወሰኑ በ2007 ዓ/ም እመጓ፣በ2009 ዓ/ም ዝጎራ፣በ2010 ዓ/ም ደግሞ መርበብት በሚሉ ርዕሶች ሦስት ልቦለድ ነክ ነገርግ ታሪክን፣ ባህልን፣ በመንፈሳዊነትን ሚስጥራዊነትን፣ሳይንስን የሚያጣቅሱ መጽሀፎችን ለህትመት በማብቃት በኢትዮጵያ ሥነ-ፅሁፍ አሻራቸዉን አስቀምጠዋል።

 ትዉልድና ዕድገታቸዉ በገጠሩ የሀገሪቱ ክፍል በመሆኑም የአደጉበትን አካባቢ ባህል፤የሞራል ዕሴት ፣ለትምህርት በዉጭ ሀገር በቆዩባቸዉ ዓመታዓመታትና በምርምርዎቻቸዉ እንዲሁም በንባብ ያገኙት ዕዉቀት፤ልምድና ገጠመኝ ለህብረተሰቡ ለማድረስ እነዚህ መፃህፍቶቼ ረድተዉኛል ይላሉ።
በባህሪያቸዉ በጎ ዓላሚ መሆናቸዉን የሚናገሩት ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ፤ቂም በቀልንና ጥላቻን በመፃፍ ነዉርን ለህብረተሰብ ከማከፋፈል ይልቅ ፤የህብረተሰቡን የሞራል ዕሴቶች የሚጠብቁ ተስፋን የሚዘሩ የማህበረሰቡን ህፀፅ የሚነቅሱ ፤ትዉልድን የሚገነቡ ጉዳዮች ላይ አትኮሮ መጻፍ ለመጭዉ ትዉልድና ለሀገር ግንባታ ይጠቅማል የሚል እምነት አላቸዉ። ያ ከሆነ ከዛሬ የተሻለች ኢትዮጵያን ለትዉልድ ማስረከብ ይቻላልም ይላሉ። ይህንን ዕምነታቸዉንም በዕለትተዕለት ህይወታቸዉና በተለያዩ መድረኮች ተጋብዘዉ ባደረጓቸዉ ንግግሮች ጭምር ሲያንፀባርቁ ይታያሉ።

ፀሐይ ጫኔ 

አዜብ ታደሰ 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች