ቆይታ ከአርቲስት ንብረት ገላዉ ጋር | ባህል | DW | 14.01.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ቆይታ ከአርቲስት ንብረት ገላዉ ጋር

የአገር ቤት የአነጋገር ለዛ ያላቸዉን ገፀ-ባህሪያት ወክሎ በመጫወት ይበልጡኑ የሚታወቅ ቢሆንም፤ ላለፉት 20 አመታት በተለያዩ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ድራማዎች እንዲሁም በመድረክ ቲያትሮች በርካታ ገፀ-ባህሪትን ወክሎ ሲተወን ቆይቷል። ድራማዎችን ይፅፋል። ያዘጋጃልም። በግል ጋዜጣና በመጽሄቶች ላይም በሪፓርተርነትና በአዘጋጅነት መስራቱን ይናገራል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:01

«የጥበብ ሰዎች ግብረ-ገብነትን መስበክ አለባቸዉ» - አርቲስት ንብረት ገላዉ

የአገር ቤት የአነጋገር ለዛ ያላቸዉን ገፀ-ባህሪያት ወክሎ በመጫወት ይበልጡኑ የሚታወቅ ቢሆንም፤ ላለፉት 20 አመታት በተለያዩ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ድራማዎች እንዲሁም በመድረክ ቲያትሮች  በርካታ ገፀ-ባህሪትን ወክሎ ሲተወን ቆይቷል። ድራማዎችን ይፅፋል። ያዘጋጃልም። በግል ጋዜጣና በመጽሄቶች ላይም በሪፓርተርነትና  በአዘጋጅነት መስራቱን ይናገራል። በተለይ አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ በርካታ ፅሁፎችን ማቅረቡንም አጫዉቶናል።ለዚሁ ስራዉ ይረዳዉ ዘንድም የምልክት ቋንቋ እስከመማር ደርሷል። «እከ» በሚለዉ የገፀ-ባህሪ ስሙ ብዙዎች ያዉቁታል። የዛሬዉ የመዝናኛ ዝግጅት እንግዳችን የጥበብ ሰዉ ንብረት ገላዉ ነው። ሙሉ ዝግጅቱን ለማድመጥ የድምጹን ማዕቀፉን ይጫኑ።

ፀሀይ ጫኔ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic