ቃለ ምልልስ ከደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጋር | ኢትዮጵያ | DW | 18.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ቃለ ምልልስ ከደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጋር

አምባሳደሩ ታግተው ከተወሰዱት ህፃናት መካከል በሁለቱ ሃገራት የጋራ ጥረት የተወሰኑት ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን ተናግረው የተቀሩትን ለማስመለስ ደግሞ አሰሳው መቀጠሉን አስታውቀዋል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:19
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:19 ደቂቃ

ቃለ ምልልስ ከደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጋር

በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጀምስ ፒትያ ሞርገን የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ግንኙነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቁ ። የሹመት ደብዳቤያቸው በቅርቡ ያቀረቡት አዲሱ አምባሳደር ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ከደቡብ ሱዳን ተሽግረው ጋምቤላ በገቡ ታጣቂዎች ከሳምንታት በፊት የተፈፀመውን ግድያ እገታ እና ዘረፋ አውግዘዋል ። አምባሳደሩ በዚሁ ጥቃት ታግተው ከተወሰዱት ህፃናት መካከል በሁለቱ ሃገራት የጋራ ጥረት የተወሰኑት ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን ተናግረው የተቀሩትን ለማስመለስ ደግሞ አሰሳው መቀጠሉን አስታውቀዋል ። ያነጋገራቸው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic