ቃለ መጠይቅ ከፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ የሃይድሮ ፖለቲክስ ተመራማሪ ጋር
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 5 2017የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ (CFA) ከእሑድ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀመሯል።
የናይል ወንዝ ተፋሰስ ሀገሮች ጉባኤ ያለስምምነት ፊርማ መጠናቀቁየናይል ወንዝ አጠቃቀምና አስተዳደር በሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፍ እንዲመራ የሚያስችል ነው የሚባልለት ይህ ማዕቀፍ የናይል ኮሚሽንን በማቋቋም ያንን ተፈፃሚ ያደርጋል። ይህንኑ አስመልክቶ በ X መልዕክት ያሰፈሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሂደቱን "የናይል ውኃን ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የተደረገው ረጅም ጉዞ ፍጻሜ" አድርገው ጠቅሰዋል።
የወንዙ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ግብጽ እና ሱዳን ማዕቀፉ የዓለማቀፍ ሕግጋት እና መርሆዎችን ያላከበረ መሆኑን በመጥቀስ ውድቅ ያደረጉት ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ግን "የጋራ የልማትና የአካባቢያዊ ውህደት ዓላማችንን ለማሳካት" የሚያግዘውን ይህንን ማዕቀፍ እንድትቀላቀሉ ሲሉ ሕጉን ላልፈረሙት ሀገራት በፊርማቸው እንዲያፀድቁት ጠይቀዋል።
የኢንቴቤ ስምምነት ተብሎ የሚታወቀውና በናይል ተፋሰስ ሀገሮች መካከል ልዩነት የፈጠረው የውኃ አጠቃቀም የስምምነት ማእቀፍ "እያንዳንዱ የናይል ተፋሰስ ሀገር በግዛቱ ውስጥ የናይል ወንዝ ውኃን የመጠቀም መብት" የሚሰጥ ነው። ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀም እንዲኖርም ያግዛል።
ደቡብ ሱዳን የናይል ወንዝ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍን ከሁለት ወራት በፊት ተቀብላ ማጽደቋን ተከትሎ ማዕቀፉ ከትናንት ጀምሮ ወደ ተግባር መለወጡ ተነግሯል።
ሆኖም ግብጽ እና ሱዳን ይህ እርምጃ የዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን የሚጥስ መሆኑን በመጥቀስ እንደማይቀበሉት መግለፃቸው ተዘግቧል። ዶቼቬለ በጉዳዩ ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሃይድሮ ፖለቲክስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ጋር አጭር ቃለ መጠይቅ አድርጓል።
ሰለሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ