ቃለ- መጠይቅ ከአምዳሳደር ግሩም አባይ ጋር  | ኢትዮጵያ | DW | 15.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

 ቃለ- መጠይቅ ከአምዳሳደር ግሩም አባይ ጋር 

የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሃገሪቱ ዉስጥ የሚካሄደዉን ተሃድሶ ከማራማድና ግድጋፍ ከማድረግ አንጻር ሙሉ ትኩረት እያደረገ መሆኑን ቤልጅየም እና በአውሮጳ ህብረት የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ግሩም ዓባይ አስታወቁ። አምባሳደር ግሩም ለዉጡ በዉጭ በተለያየ ቦታ ከሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ ጋር በበለጠ በቅርበት እንድንሰራ እድል ፈጥሮልናል ብለዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:22

ቃለ መጠይቅ ከአምባሳደር ግሩም አባይ ጋር

አምባሳደር ግሩም ዓባይ ከ «DW» ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ለዉጡ ኤምባሲዉ ከተወከለበት ሃገር እና ተቋማት ጋር ከዚህ ቀደም የነበረዉ ሻካራ ጉዳዮች እንዲወገዱ በማድረጉ የበለጠ የተሳለጠ ሥራ እንድንሰራ እንዲሁም የኢትዮጵያዉያኑንም የምናገኝበትን እድልም ከፍቶልናል ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የሚመሩት መንግስት ሥልጣን ከያዘ ወዲሕ ኢትዮጵያ ከምዕራባዉያን መንግሥታት ጋር ያላት ግንኙነት ከበፊቱ ይበልጥ የተጠናከረ መሄዱን አምባሳደሩ በቃለ ምልልሱ ጠቁመዋል። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ በቤልጅየም እና በአውሮጳ ህብረት የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ግሩም ዓባይን አነጋግሮአቸዋል። 

ገበያው ንጉሴ 

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ
 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች