ቁጣ የቀሰቀሰዉ ወሲባዊ ጥቃት በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 24.11.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ቁጣ የቀሰቀሰዉ ወሲባዊ ጥቃት በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የሚፈጸመውን ወሲባዊ ጥቃት አሳሳቢ ነው ተባለ። በ17 ዓመቷ ታዳጊ ሐና ላላንጎ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሞባት ህይወቷ ካለፈ በኋላ ድርጊቱ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል።


የ10ኛ ክፍል ተማሪ እና የ17 ዓመት ታዳጊ ነበረች። አዲስ አበባ ውስጥ ከአየር ጤና ወደ ጦር ኃይሎች ልትጓዝ በተሳፈረችበት ሚኒባስ ታክሲ ውስጥ በነበሩ አምስት ሰዎች ታፍና ተወስዳ በተደጋጋሚ በመደፈሯ ለሞት የተዳረገችው-ሐና ላላንጎ። ታዳጊዋን አፍነው በመውሰድ ደፍረዋል በሚል የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው በምርመራ ላይ ናቸው። በሐና ላላንጎ ላይ የተፈጸመው ወሲባዊ ጥቃት በመገናኛ ብዙሃን ይፋ ከሆነ በኋላ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል።
ከነገ ጀምሮ ለ16 ቀናት የሚወሳዉ የጾታዊ ጥቃት ዘመቻ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ ከተነሱ የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮች አንዱ በሐና ላላንጎ ላይ የተፈጸመው ወሲባዊ ጥቃት ነበር። በውይይቱ ላይ የተገኙት የታዳጊዋ ቤተሰቦች በሀዘን ተጎድተዋል ሲሉ የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ሃላፊ ወ/ሮ ዜናዬ ታደሰ ተናግረዋል።
ወሲባዊ ጥቃትን ጨምሮ ሴቶችን በተመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚሰራው የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር የህግ ድጋፍ ለሚፈልጉ የማማከር እና ድጋፍ አገልግሎት ይሰጣል። ማህበሩን በበላይነቲ የሚመሩት ወ/ሮ ዜናዬ ታደሰ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት አሳሳቢ መሆኑንና ትኩረት እንደሚያሻው ተናግረዋል።


እሸቴ በቀለ
ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic