ቁንጅ እና ፊትን ማቅላት | ወጣቶች | DW | 30.03.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ወጣቶች

ቁንጅ እና ፊትን ማቅላት

አፍሪቃ ውስጥ ቁንጅናን በቅላት የሚገልፁ በርካታ ሰዎች አሉ። ለዚህም ሲሉ በተለይ ወጣቶች የተለያዩ ቅባቶችን እየተጠቀሙ ፊታቸውን ለማቅላት ይሞክራሉ። #77ከመቶው የተሰኘው የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ትኩረት ቁንጅናን እና የሚያስወጣውን ገንዘብ ይመለከታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:05

ቁንጅ እንዴት ይገለፃል?

ከአፍሪቃ ሕዝብ 77 ከመቶ የሚሆነዉ ዕድሜዉ ከ35 ዓመት በታች የሆነ ወጣት ነዉ ተብሎ ይገመታል። ወጣቱን አፍሪቃዊ ከሚያሳስቡት ነገር አንዱ ደግሞ ቁንጅና ነው። ግን ቁንጅና እንዴት ይገለፃል? ሙሽሮች የሰርጋቸው ዕለት ያምራሉ አይደል? ነገር ግን ውዱ አልባሳት፣  ጌጣ ጌጥ እና ድግሱን ትተው ቀለል አድርገው ወጪ ሳያበዙ ቢጋቡስ? ይህንን ነው የተወሰኑ ጥንዶች ሴኔጋል ውስጥ ያደረጉት።

ከዚህም በተጨማሪ  ኢትዮጵያውያን የዝግጅታችን ተከታታዮቻችን ለቁንጅና ሲባል የተለያዩ ቅባቶችን እየተጠቀሙ የፊትን ቆዳ ለማቅላት መሞከር አስፈላጊ መሆን ወይም አለመሆኑን ጠይቀናል? እነሱስ ውበትን  እንዴት ይገልፁታል?  ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በአንድ ቁንጅና ማዕከል የምትሰራው የያስሚን እናት « የኛ ሰዎች ለመቅላት ብለው የሚያደርጉት ነገር ፊታቸው ላይ ብዙ ጉዳት አድርሶባቸዋል። ይህ የሚያሳየው ደግሞ በማንነታቸው ያለመተማመን እና ያለ ሙኩራትን  ነው» ትላለች።

Afrika Folgen von Skin-Bleaching

ቆዳን የሚያቀላ ቅባት ያስከተለው ጠባሳ

ኢትዮጵያ የሚኖረው ወጣት ደረሰ ዳምጠው ደግሞ ቁንጅናን እንዲህ ይገልፀዋል። « ውበት ተፈጥሮ በለገሰችው እና በውስጣዊ ማንነት ነው ለኔ የሚገለፀው።»

ሙሉጌታ ገብረ ፃዲቅ በፌስ ቡክ፤ በተለይ እኔ ባልሁበት ኣረብ ኣገር፤ ሳውዲዎችን እያዩ ዱቄት የሚለቀለቁ ስፍር ቁጥር የላቸውም።» የሚል አስተያየት ልኮልናል። ሌላ አስተያየቷን ያካፈለችን ወጣት ኤደን ወርቁ ትባላለች። እሷ በምትኖርበት ሀገር ኩዊት ማዲያት ወይም ጠባሳ ያለባቸው ሴቶች ይህንን የሚያጠፋላቸው ወይም የሚሸፍኑበት ሜካፕ ይቀባሉ እንጂ ፊታቸውን ሆን ብለው ለማቅላት ሌላ ነገር ሲቀቡ አልታዘብኩም ብላናለች። ለእሷ ቅላት የውበት መለኪያ አይደለም። « በብዛት የሀገራችን ፊልሞች እና ድራማዎች የሚሰሩት ቀላ ባሉ ሰዎች ነው እንጂ በጥቁር ቆንጆዎች አይደሉም። እኛን ደግሞ የሚስበን የምናየው ነገር ነው።»

 

200 የሚጠጉ ወጣት ሴኔጋላውያን ወጪን ለመቀነስ በቡድን የፈፀሙት ሰርግ

ምናልባትም ሴቶች ከወንዶች ይልቅ በሰርጋቸው ቀን አምረው ተውበው ለመታየት ፤ ለቬሎ ፣ ለሜካፕ እና ጌጣ ጌጦች ብዙ ገንዘብ ያወጣሉ። ነገር ግን ለዚህ ሁሉ ወጪ ገንዘብ ከሌለስ? 200 የሚጠጉ ወጣት ሴኔጋላውያን በቡድን ሆነው ሰርጋቸውን ፈፅመዋል። ወጪያቸው ሲመነዘር 700 ብር ገደማ ነው የፈጀው ትላለች በሰርጉ ላይ የተገኘችው ባልደረባችን ኢማኑኤለ ላንዲያስ በላከችው ዘገባ ።

የሰርጉ ዕለት የሙሽሪት ቤት ፀጥ ረጭ ያለ ነው። የሰርገኞች ቤት የተለመደው ግርግር እና ሽርጉድ አይታይም። ዛሬ የቤቱ የመጀመሪያ ልጅ የሆነችው የ 26 ዓመቷ ማጉቴ ንድዬ ሰርግ መሆኑን ከግቢ ውጭም ይሁን ውስጥ የሚጠቁም ነገር የለም። ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ግን የልጅነት አብሯአደጓ ከሆነው ፍቅረኛዋ ጋር ትዳር ትመሰርታለች። « ሜካፔን እቀባ እና ማህበረሰቤን የሚወክለውን ነጭ ቀሚሴን እለብሳለሁ። የሚያምር ነጭ ቀሚሴን እና ቬሎ አደርጋለሁ። ከዛም ትዳሩ ይፋ እስከሚሆን ድረስ የእናቴ አልጋ ላይ ሆኜ እጠብቃለሁ።»

ማጌት ወላጆቿ ባለትዳር ሴት መሆኗን አውጀው እስኪመለሱ ከሁለት ጓደኞቿ ጋር ሆና እቤት ውስጥ ትጠብቃለች። « የሰርጌ ዕለት ነው ዛሬ።  እንደሚድሩኝ ይፋ ለማድረግ የሄዱት ወላጆቼ እስኪመለሱ እየተጠባበኩ ነው። ከሌሎች ብዙ ሰዎች ጋር በዚህ አይነት ሁኔታ ትዳር መፈፀሜ ያስደስተኛል። ተምሳሌት የሚሆን ዕለት ነው።»

በባህሉ መሰረት እያንዳንዱ ቤተሰብ በሙሽርዋ ስም ወደ መስጊድ ተወካይ ይልካል። እስከዚያው ሙሽሪት እና ሙሽራው በየቤታቸው ሆነው ይጠብቃሉ።« ወንዶቹ አብረው ይሆናሉ። እኛ ሴቶቹ ደግሞ እዚህ ሆነን እንጠብቃለን።ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ባለ ትዳር ናችሁ የሚለው መልዕክት እስኪደርሰን ድረስ ማለት ነው።»

 በቡድን ሆኖ በላየኔ ማህበረሰብ ትዳር መፈፀም በመስራቹ ዘንድ ብቻ ሳይሆን የሚበረታታው ባህሉ ወጣት ትዳር መስራቾች ያለ ተጋነነ ወጪ እና ብድር የትዳር ህይወታቸውን መመስረት የሚያስችል ስለሆነ ይደግፉታል። በጠቅላላው 700 ብር ገደማ የሚሆን ጥሎሽ ለሁለቱም ቤተሰቦች እና መስጊድ ይሰጣል። ከዛ ባለፈ ድግስ፣ እንግዳ ወይም ስጦታ የለም። « ወጪ ለመቀነስ ነው። ቀለል ያለ ነገር እወዳለሁ። ያለ ትልቅ ድግስ ከጓደኞቼ እና ቤተሰቦቼ ጋር ሰብሰብ ማለት መቻሌ ያስደስተኛል። ግዙፍ የሆነ ሰርግ አስደስቶኝ አያውቅም። ፈጣሪ ልመናዬን የሰማ ይመስላል። »ትላለች ማጌት። ወጣቷ ለህይወቷ የምትፈልገውን ጠንቅቃ የምታውቅ ይመስላል። « ትዳር ገንዘብ ወይም ብልፅግና ብቻ አይደለም። ይህንን ነው ተስፋ የምናደርገው ወይም እንዲኖረን የምንፀልየው። ነገር ግን ትዳርን ዘለቄታማ የሚያደርገው ይህ አይደለም።»

የማጌት ጓደኛ ራማቱ፤ የጓደኛዋ ሰርግ በዚህ አይነት መንገድ መፈፀሙ ብዙም አያስደንቃትም። «ዛሬ ጓደኛችንን ለማገዝ ስንል ነው የመጣነው። የኔ ሰርግ ያለፈው ሳምንት ነበር።እኔ ግዙፍ ሰርግ ምርጫዬ ነበር። እሷ ደግሞ ቀለል ያለ ነገር ነው የመረጠችው። ውሳኔዋን እቀበለዋለሁ።»ራማቱ እንደ አብዛኞቹ ወጣት ሙሽሮች ድል ያለ ሰርግ ምኞቷ ነበር።

« ከልጅነቴ አንስቶ እመኘው የነበረ ነው። ብቻዬን የምወጣው አልነበረም። ነገር ግን በቤተሰብ ድጋፍ የተመኘሁትን ሰርግ አግኝቻለሁ ማለት እችላለሁ። ከ 200 በላይ ሰዎች ነበሩ። ዘመድ አዝማድ፤ጓደኞች ፣ጎረቤቶች! ብቻ ጭንቅንቅ ያለ ነበር።»

ገንዘብ ለሰርግ ትልቅ ሚና ይጫወታል። በቂ ገንዘብ የሌላቸው ጥንዶች ለአመታት ገንዘብ ያጠራቅማሉ ወይም ደግሞ ብድር ይወስዳሉ ይላል ባሲሮ ላሲሳ። የ 29 ዓመቱ ሙሽራ ከወደፊት ባልተቤቱ 1 ኪ ሜትር በማይሞላ ርቀት ላይ ሆኖ ከጓደኞቹ ጋር ወላጆቹ እስኪመለሱ እሱም በፊናው ይጠባበቃል። « ትዳር ከመመስረት ሌሎችን የሚያግዳቸው ብዙውን ጊዜ ልጃቸውን ለትዳር የሚሰጡት ቤተሰቦች ከፍተኛ መጠን ያለው ጥሎሽ ስለሚጠይቁ ነው። ከ 50 000 ብር በላይ!  ለዛ ስንል ነው እኛ ጥሎሹን በ 700 ብር ገደማ እንዲሆን የወሰነው።»

ኢማኑኤለ ላንዲያስ/ ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች