ቀዝቃዛዉ የትራምፕና የሜርክል ወዳጅነት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 27.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ቀዝቃዛዉ የትራምፕና የሜርክል ወዳጅነት

የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ከዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመነጋገር ዋሽንግተን ገብተዋል። ሜርክል ዛሬ ዋሽንግተን የደረሱት የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮ የዋሽንግተን ጉብኝታቸዉን እንዳጠናቀቁ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:25

መራሒተ መንግሥትዋ ለጉብኝት ዋሽንግተን ይገኛሉ።


ትራምፕ የፈረንሳዩን ፕሬዚደንት በደማቅ ሲቀበልዋቸዉና በደስታ ሲያናጋሩዋቸዉ ቆይተዉ፤ ብዙም ወዳጅነት የሌላቸዉን የጀርመንዋን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልን በምን ሁኔታ አቀባበልና መስተንግዶ ያደርጉላቸዋል የሚለዉ ነጥብ በጀርመን የመነጋገርያ ርዕስ ሆኖ ነዉ የሰነበተዉ። የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ግንኙነት እንደቀድሞዉ ዘመናት ወዳጅነታቸዉ ልባዊ እና ሞቅ ያለ መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች እና ጋዜጠኞች በተለያዩ ዘገባዎቻቸዉ ጠቅሰዋል። የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልም ሆኑ የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመካከላቸዉ ያለዉ ወዳጅነት ደመና ያጠላበት መሆኑን ጠንቅቀዉ ያዉቁታል።  እንድያም ሆኖ ሁለቱም መሪዎች በሃገራቱ መካከል ያለዉን ትስስር በተመለከተ ሊወያዩባቸዉ የሚገባ በርካታ ነጥቦች እንደሚጠብቁዋቸዉ ያዉቃሉ።  ከመነጋገርያ ነጥቦቹ መካከል በተለይ ትራምፕ በአዉሮጳ ላይ ያነሱት የንግድ ዉዝግብ ተጠቃሽ ነዉ። የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ይነጋገሩባቸዋል የተባለዉን አጀንዳ አስመልክቶ የዶቼ ቬለዋ ሚሻኤል ኪንፈር የዘገበችዉን ይልማ ኃይለሚካኤል  

ይልማ ኃይለሚካኤል /  ሚሻኤል ኪንፈር 

አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች