ቀኝ ፅንፈኛው « አማራጭ ለጀርመን » እና አወዛጋቢው መርሃ ግብሩ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 02.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ቀኝ ፅንፈኛው « አማራጭ ለጀርመን » እና አወዛጋቢው መርሃ ግብሩ

የገንዘብ ኪሳራ ለደረሰባቸው የአውሮጳ ህብረት አባል ሃገራት ብድርና እርዳታ መሰጠቱን በመቃወም የዛሬ ሦስት ዓመት የተመሰረተው ይኽው ፓርቲ በጀርመን ፣የሙስሊሞች የፀሎት ጥሪ እና ሴቶች ፊታቸውን መሸፈናቸው እንዲቆም በትምህርት ቤቶችም ራስን መከናነብ እንዲታገድ ጠይቋል ።

«አማራጭ ለጀርመን» የተባለው የጀርመን ቀኝ ፅንፈኛ ፓርቲ ባለፈው እሁድ የሁለት ቀናት ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ ፀረ እስልምና መርህ ያካተተውን መርሃ ግብሩን ይፋ አደርጓል ። ፓርቲው በዚሁ መርሃ ግብሩ «እስልምና የጀርመን አካል አይደለም » ሲል ከማስቀመጡም በተጨማሪ ስደተኞች ወደ ጀርመን መግባታቸው እንዲገደብ ጠይቋል፣ የአውሮጳ ህብረትም ብዙውን ስልጣኑን ለብሔራዊ መንግሥታት እንዲመልስ፣ ይህን ካላደረገ ግን ጀርመንን ከህብረቱ እና ከዩሮ ቀጣና እንደሚያስወጣም አስታውቋል። የገንዘብ ኪሳራ ለደረሰባቸው የአውሮጳ ህብረት አባል ሃገራት ብድርና እርዳታ መሰጠቱን በመቃወም የዛሬ ሦስት ዓመት የተመሰረተው ይኸው ፓርቲ በጀርመን የሙስሊሞች የፀሎት ጥሪ እና ሴቶች ፊታቸውን መሸፈናቸው እንዲቆም በትምህርት ቤቶችም ራስን መከናነብ እንዲታገድ ጠይቋል ። የበርሊኑ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ አለው ።


ይልማ ኃይለ ሚካኤል


ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic