ሽፈራዉ /ሃለኮ/ ተክል | ጤና እና አካባቢ | DW | 03.03.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ሽፈራዉ /ሃለኮ/ ተክል

በሳይንሳዊ ስሙ ሞሪንጋ ስቴኖፔታል፤ በአገርኛዉ ደግሞ በአንዳንድ አካባቢ ሽፈራዉ፤ በሌላዉ ስፍራ ሃለኮ፤ በሌሎች ስፍራዎችም ሌሎች ስያሜዎች አሉት። ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚሰጥ የድሃ ወገን የሆነ ተክል ነዉ ይሉታል ያጠኑት ባለሙያዎች።

...እዚህም መትከል ይቻላል...

....እዚህም መትከል ይቻላል...

ቅጠሉና ፍሬዉ ለምግብነት ከመዋሉ ባሻገር፤ ቅርፊትና ስራስሩ ሳይቀር ለመድሃኒትነት ይበጃል። ለመብቀል እጅግም ዉሃ አይፈልግም። በደረቅና ርጥበት በሌለበት የአየር ጠባይ አሳምሮ ይበቅላል። ይህ ተክል የሚሰጠዉ ጥቅም ከፍተኛ ሆኖ ሳላ በአገራችን ኅብረተሰቡ በቅጡ ምንነቱን ስላላወቀለት ትኩረት አላገኘም።